Saturday, 12 March 2016 11:47

አዲስ ብድርና ቁጠባ፤ ከ968 ሚ. ብር በላይ ብድር ሰጥቻለሁ አለ

Written by  ማህሌት ኪዳነወልድ
Rate this item
(1 Vote)

በ6 ወር ውስጥ ከ658 ሚ. ብር በላይ በቁጠባ ተሰባስቧል
                              
       የህብረተሰቡ የቁጠባ ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የገለፀው የአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አክሲዮን ማህበር፤ በዘንድሮ ግማሽ ዓመት ከ658 ሚ. ብር በላይ በቁጠባ ማሰባሰብ እንደተቻለ ጠቁሟል፡፡
የማህበሩ የኮሚዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ምዕራፍ አለማየሁ ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፤ በግማሽ ዓመቱ ከ658 ሚ. ብር በላይ በቁጠባ የተሰበሰበ ሲሆን፤ ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ11 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ የቁጠባው የገንዘብ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣት ድርጅቱ የሚያበድረውን ገንዘብ ከቁጠባ እንዲሸፍን አስችሎታል ያሉት ወ/ሮ ምእራፍ፤ ባለፉት 6 ወራት የብድሩን 64 በመቶ ከቁጠባ መሸፈኑን ለመሸፈን መቻሉን ገልፀዋል፡፡
ቁጠባ የአገር ኢኮኖሚ መሰረት መሆኑ አያጠያይቅም ያሉት ኃላፊዋ፤ እንደ ግለሰብም የህይወትን እቅድ ለማሳካት ከሚያገኙት ነገር ላይ መቆጠብ አይነተኛ መፍትሄ ነው ብለዋል፡፡
ተቋሙ በግማሽ ዓመቱ ከ17 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተበዳሪዎች ከ968 ሚ. ብር በላይ ብድር መስጠቱን ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡ ተበዳሪዎቹም በንግድ፣ በአገልግሎት፣ በኮንስትራክሽን፣ በማኑፋክቸሪንግና መሰል የሥራ ዘርፎች የተሰማሩና ሊሰማሩ ያቀዱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የድርጅቱ የቁጠባ አወጣጥ ስርአት ደንበኞችን እንደሚያመላልስ፣ ደንበኞች የቁጠባ መጠናቸውን እንዲያሳድጉ የሚደረገው የማሳመን ጥረት አነስተኛ እንደሆነና ሌሎች መሰል ችግሮች መኖራቸውን አረጋግጫለሁ ያለው ተቋሙ፤ በቀጣይ ችግሮችን ለመፍታት ጠንክሮ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

Read 3008 times