Saturday, 26 March 2016 11:55

የደረጀ በላይነህ “የደመና ሳቆች” ለገበያ ሊቀርብ ነው

Written by  በማህሌት ኪዳነወልድ እና ናፍቆት
Rate this item
(4 votes)

 በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በተከታታይ ሂሳዊ ጽሑፎችን በማቅረብ የሚታወቀው ደራሲና ገጣሚ ደረጀ በላይነህ የፃፈው “የደመና ሳቆች” የተሰኘ ረዥም ልብወለድ በመጪው ሳምንት ለገበያ ሊቀርብ ነው፡፡
የመፅሃፉ ጭብጥ በብላቴ አየር ወለድ ማሰልጠኛ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ወታደራዊ ዘመቻ ላይና በወጣትነት የፍቅር ግጥምጥሞሽ ላይ ያጠነጥናል ተብሏል፡፡ መቼቱን ብላቴ፣ ተፈሪ ኬላ (ሲዳማ) እና ወላይታ ሶዶ ከተሞች ላይ ያደረገው ልብወለዱ፤በ230 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ58 ብር ለገበያ ይቀርባል፡፡ የመጽሃፉ አሳታሚና አከፋፋይም ጃፋር የመጻሕፍት መደብር መሆኑ ታውቋል፡፡
ደራሲው ከዚህ ቀደም በተለያዩ ዘውጎች 7 መፃህፍትን ለንባብ ያበቃ ሲሆን ከእነዚህም መካከል “ብልጥ ጀንበር”፣ “የዕድሜ መንገድ”፣ “የአዳም ድንኳን” እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ ደረጀ በላይነህ በብስራት 101.1 ኤፍ ኤም ራዲዮ “አዲስ ምዕራፍ” የተሰኘና በናሁ ቴሌቪዥን “የኔታ” የሚል ፕሮግራም ከሙያ አጋሮቹ ጋር በማቅረብም ይታወቃል፡፡

Read 3460 times