Saturday, 28 May 2016 15:19

“ግንቦት 20፣ ቅድመ ምርመራን በማስቀረት ደራሲያንን እፎይ አሰኝቷል

Written by  (ስማቸውን ያልገለፁ ደራሲ)
Rate this item
(0 votes)

ግንቦት 20 ለደራሲው ከፍተኛ ለውጥ አምጥቷል፡፡
ከእነዚህም አንዱ በደራሲያን ጫንቃ ላይ ትልቅ ሸክም የነበረውን ቅድመ ምርመራ ማስቀረቱ ነው፡፡
ይህን ቅድመ ምርመራ የሚያስቀር አዋጅ መውጣቱ በተለይ ለደራሲያን ትልቅ ነገር ነው፡፡ ጋዜጠኛን ወይም ሙዚቀኛን አይመለከትም፡፡ ደራሲያንን ብቻ ነው፡፡ ዛሬ ደራሲያን የፃፍነውን ጽሑፍ ይዘን በቀጥታ ማተሚያ ቤት በመሄድ የፈለግነውን እናሳትማለን፡፡ ይህንን እድል እንደ ቀላል ነገር ማየት ትክክል አይመስለኝም፡፡ በሌላው ዘርፍ ስንመለከት ደግሞ ይሄው ሳንሱር በጣም አደገኛ ነው፡፡ እንዴት ብትይ… በቴአትሩ፣ በፊልሙና በሌሎች ዘርፎችም እየተተገበረ ነው፡፡ ከህገ- መንግስቱ ውጭ የራሳቸውን አዋጅ አውጥተው የሚያፍኑ ሀይሎች ተፈጥረዋል፡፡
ለምሳሌ ቴአትር ለማሳየት ባህልና ቱሪዝም ገምግሞ ካላሳለፈሽ ማሳየት አትችይም፡፡ ፊልም ሰርተሽ ባህልና ቱሪዝም ፈቅዶልሽ፣ የግል ሲኒማ ቤት ስትሄጂ “የኔን ደረጃ አይመጥንም” ይሉና ወገብሽን ቆርጠው ይልኩሻል፡፡ ምን እንደሚፈለግ አይታወቅም፡፡ አንዱ ዘርፍ የቅድመ ምርመራ ሲዘጋ፣ በሌሎች ዘርፍ በርካታና ልንቋቋማቸው የማንችለው ቅድመ መርማሪዎች ተፈጥረዋል፡፡  በየትኛውም ዓለም መንግስት ለእንደዚህ አይነት ተቋማት በተለይም የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና ያዳብራሉ ለሚባሉ ነገሮች ድጋፍ ያደርጋል፡፡ እኛ አገር ይሄ ድጋፍ የለም፡፡ ይህንን ድጋፍ የማይሰጥ መንግስት ደግሞ ራሱም አይጠቀምም፡፡ ኢህአዴግ ከጫካ ጀምሮ ታጅቦ የገባው በኪነ-ጥበብ ነው፡፡ በእነ እያሱ በረኸ ኪነ-ጥበብ ነው ታጅቦ እስከ ቤተ - መንግስት የገባው፡፡ ከዚያ በኋላ በኪነ -ጥበቡ እንዴት ልጠቀምበት አላለም፡፡
 በአጠቃላይ እኔ እንደ ደራሲ፤ የቅድመ ምርመራው ከመቅረቱ በቀር በርካታ ችግሮች አሉ ባይ ነኝ፡፡

Read 942 times