Monday, 29 August 2016 10:44

የደራሲያን ማህበር “ብሌን” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በአንጋፋው የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በየስድስት ወሩ እየተዘጋጀ ለንባብ የሚበቃው “ብሌን” መፅሄት በልዩ አቀራረብ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መፅሄቱ ከቀድሞው አቀራረብ በተለየ መልኩ በጥናታዊ ፅሁፎች እየዳበረ መውጣት ከጀመረ የአሁኑ አራተኛ እትሙ እንደሆነ ማህበሩ ገልጿል፡፡ በብሌን ውስጥ ከተካተቱ በርካታ ፅሁፎች መካከል በስነ-ህይወት ገዛኸኝ የቀረበው፤“ባይተዋርነት በሰባተኛው መልአክ፣ በትኩሳትና በሌቱም አይነጋልኝ ውስጥ”፣ በአቦነህ አሻግሬ ዘየሱስ የተጻፈው፤“ስለ ኢትዮጵያ ቴአትር አጀማመር እና የመጀመሪያው ተውኔት”፣ የታደሰ እሱባለው፤“የግዕዝ ሆሄያትና ስነ-ግጥም በእንዚራ ስብሀት መፅሀፍ”፣ በውቤ ካሳዬ የተሰናዳው፤ “የኢትዮጵያ ረቂቅ ሙዚቃ ኦርኬስትራ ታሪክ አጭር ቅኝት” እና ከአንጋፋዋ ደራሲ ፀሐይ መላኩ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ይገኙበታል፡፡ መፅሄቱ፤ “የቃቄ ውርደት” በተሰኘው ሙዚቃዊ ድራማ ላይም የተሰራ ግምገማም አውጥቷል፡፡ በ101 ገጾች የተቀነበበው  “ብሌን” መፅሄት በ50 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡  

Read 1145 times