Saturday, 03 September 2016 11:54

‹‹ሌላ ቀን›› ፊልም ትላንት ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲና ዳይሬክተር ይድነቃቸው ብርሃኑ ተፅፎ የተዘጋጀው ‹‹ሌላ ቀን›› የተሰኘ ፊልም ትላንት ምሽት በሀርመኒ ሆቴል ተመረቀ፡፡ የድራማ ዘውግ ያለው ፊልሙ የ1፡30 ሰዓት ርዝመት እንዳለውና ተሰርቶ ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት እንደፈጀ ታውቋል። በፊልሙ ላይ ፍቅርተ ደሳለኝ፣ ሰለሞን ታሼ (ጋጋ)፣ ብሩክታዊት ለማ፣ ሰብለ ወርቁና ሌሎችም አንጋፋና ወጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል፡፡ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ለመታደም የመግቢያ ዋጋው አንድ መቶ ብር የነበረ ሲሆን  ፊልሙን ፕሮዲዩስ ያደረገው የሺ ብርሃን ፊልም ፕሮሞሽን ነው ተብሏል፡፡

Read 828 times