Saturday, 03 September 2016 12:02

‹‹ሊዮ እና ርብቃ›› የልጆች መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ‹‹Hansel and Gretel›› የተሰኘው የእንግሊዝኛ ተረት መፅሀፍ በጋዜጠኛ ግርማ ብርሃኑ ‹‹ሊዮ እና ርብቃ›› በሚል ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ገበያ ላይ ዋለ። መፅሀፉ ሊዮ ስለተባለ ልጅና ስለ ታናሽ እህቱ ርብቃ የህይወት ውጣ ውረድ የሚተርክና ለልጆች ጥንካሬና ብልሀትን የሚያስተምር ነው ተብሎ ስለታመነበት ወደ አማርኛ መተርጎሙን የመፅሀፉ ጋዜጠኛ ግርማ ብርሃኑ ተናግሯል፡፡ ከአማርኛው ጎን ለጎን ታሪኩ በእንግሊዝኛ አብሮ የቀረበ ሲሆን መፅሀፉ የቀረበው ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ አገር ህፃናት ያገለግላል ተብሏል፡፡ በ74 ገፆች የቀረበው የተረት መፅሀፉ በ40 ብር ከ50 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 1976 times