Sunday, 09 October 2016 00:00

ሰው ስንፈልግ ባጀን” መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌን መጣጥፎች ስብስብ የያዘው “ሰው ስንፈልግ ባጀን” የተሰኘ መፅሐፍ ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ አምስት ኪሎ በሚገኘው ቅርስ ጥበቃና ጥናት አዳራሽ እንደሚመረቅ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ኢጋ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ገለፀ፡፡ ከምርቃት ሥነ ስርዓቱ ጎን ለጎን፣ የጋዜጠኛው ሙት አመትም እንደሚዘከር ተነግሯል፡፡  
ደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደ በመፅሐፉ ላይ ዳሰሳ የሚያቀርብ ሲሆን ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ እንዲሁም ሌሎች ገጣሚያንና ፀሐፍት ግጥሞችና መጣጥፎችን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ የጋዜጠኛ ሉሌን የህይወትና የስራ እንቅስቃሴ የሚያስቃኝ ዘጋቢ ፊልምም ለዕይታ ይበቃል፡፡ በበ344 ገጾች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ ለአገር ውስጥ በ81 ብር፣ ለውጭ አገራት በ30 ዶላር ይሸጣል፡፡

Read 2268 times