Sunday, 27 November 2016 00:00

“የእግዜር ድልድይ” ፊልም እየተመረቀ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    በኩላሊት ህመም ላይ አተኩሮ በሰራው “ላምባ” የተሰኘ ፊልሙ እውቅናና አድናቆት ያተረፈው የደራሲና ዳይሬክተር አንተነህ ኃይሌ አዲስ ፊልም “የእግዜር ድልድይ” ከሐሙስ ጀምሮ በተመረጡ የግል ሲኒማ ቤቶች እየተመረቀ ሲሆን በዛሬው ዕለት ምርቃቱ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡
የ1፡47 ደቂቃ እርዝመት ያለውና ከ1968 ዓ.ም እስከ አሁን ባለው ግዜ ውስጥ በእድገት በህብረት ዘመቻ ተጀምሮ የዘለቀ ፍቅር ላይ አተኩሮ የተሰራው ይህ ፊልም፤ በ40 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የነበሩ የአኗኗር ዘይቤዎችን፤ የፍቅር ሁነቶችንና አገራዊ ጉዳዮችን ይዳስሳል ተብሏል፡፡ የፍቅር ድራማ ዘውግ ባለው በዚህ ፊልም ላይ ፀጋነሽ ሀይሉ፣ ደረጃ ደመቀ፣ ሄኖክ ወንድሙና ሌሎችም ወጣትና አንጋፋ ተዋንያን መሳተፋቸውን የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር አንተነህ ኃይሌ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ በ123 ስቱዲዮና በአሀፒ ስቱዲዮ ተሰርቶ በኢንደራሴ ፊልም ፕሮዳክሽንና በሴባስቶፖል ፊልሞች የቀረበው ፊልሙ፤ በአንተነህ ሀይሌና በቴዎድሮስ ተሾመ ፕሮዲዩስ መደረጉንና 1 ሚ. ብር ገደማ መፍጀቱ ታውቋል፡፡

Read 1194 times