Sunday, 25 December 2016 00:00

‹‹ነፀብራቅ ቁጥር 2›› የስዕል ኤግዚቢሽን ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 ኪዳኔ ጌታው፣ ሰዓሊ ናትናኤል አሸብርና ሰዓሊ ዮሴፍ ሰበቅሳ የተሰሩ የስዕል ስራዎች ለእይታ የሚቀርቡበት ‹‹ነፀብራቅ ቁጥር 2›› የስዕል ኤግዚቢሽን ከምሽቱ 12፡30 ጀምሮ ከዛንቺስ በሚገኘው “ድንቅ አርት ጋለሪ” ይከፈታል፡፡ የሦስቱ ሰዓሊያን በርካታ ስራዎች ለተመልካች የሚቀርብበት ኤግዚቢሽኑ፣ ለተከታታይ 22 ቀናት ለእይታ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡
ሰዓሊዎቹ ባለፈው ዓመት “ነፀብራቅ ቁጥር 1›› በተሰኘው የስዕል ኤግዚቢሽን፤ 30 ስራዎቻቸውን በ“ታዛ አርት ጋለሪ” ለእይታ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን የስዕል ትምህርታቸውን ከ6 ዓመት በፊት በአቢሲኒያ ስነ- ጥበብ ት/ቤት ከተከታተሉ በኋላ አብረው መስራት መቀጠላቸው ታውቋል፡፡

Read 884 times