Sunday, 25 December 2016 00:00

‹‹አለመኖር›› መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(6 votes)

  በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይካትሪ ትምህርት ክፍል መምህርና የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአዕምሮ ሀኪም በሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ የተፃፈው ‹‹አለመኖር›› የተሰኘ ልብወለድ መፅሀፍ ለንባብ በቃ፡፡ ጥልቅ በሆኑ ፍልስፍናዊ እሳቤዎችና ስነ-ልቦናዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥነው መጽሀፉ፤ በህክምናና ሀኪሞች ዙሪያ ትኩረት አድርጎ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን ያነሳል ተብሏል፡፡
በልዩ ስነ-ፅሁፋዊ ውበትን እንደተፃፈ የተነገረለት መፅሀፉ፤ በ373 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ120 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በእውቀት በርና በክብሩ መፅሀፍት መደብር እየተከፋፈለ እንደሆነም ታውቋል፡፡

Read 6209 times