Sunday, 05 February 2017 00:00

“ሚስ አዲስ አበባ የጤና አምባሳደር” ተመረጠች

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ የመድሀኒትና ጤና ክብከቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን፤ ከምስክር ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር፣ “ሚስ አዲስ አበባ የጤና አምባሳደር”ን ባለፈው ሳምንት መርጠዋል፡፡
በውድድሩ የተሳተፉ 25 ሞዴሎች ላለፉት ሶስት ወራት ከጤና አጠባበቅና ከአደንዛዥ ዕፅ አስከፊነት ጋር በተያያዘ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ሲሆን ከትናንት በስቲያ በጌትፋም ሆቴል አሸናፊዋ የጤና አምባሳደርነት ማዕረጉን ወስዳለች፡፡ በምርጫ ስነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ የምግብ የመድሀኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ ጌታቸው ወረንቲን ጨምሮ በርካታ አርቲስቶች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ሞዴሎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡  
አምባሳደሯ ለቀጣዩ አንድ አመት በት/ቤቶች፣ በወጣት ማዕከላትና በተለያዩ ተቋማት በመዘዋወር ወጣቶች እንዴት ጤናቸውን መጠበቅና ከአደንዛዥ ዕፅ ጉዳት ራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ታስተምራለች ተብሏል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ የጤና አምባሳደር ሲመርጥ ያሁኑ ሁለተኛው እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በሐሙሱ የጤና አምባሳደር ውድድር ስነ-ስርዓት ላይ የፋሽን ትርኢት፣ ስታንዳፕ ኮሜዲና የሙዚቃ ዝግጅትም ቀርቧል፡፡

Read 1450 times