Monday, 06 March 2017 00:00

‹‹ዜማ ብዕር›› 10ኛ አመቱን ዛሬ ያከብራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በወጣትና አንጋፋ ሴት የሥነ- ፅሁፍ ባለሙያዎች የተቋቋመው ‹‹ዜማ ብዕር›› የሴቶች የስነ ፅሁፍ  ማህበር የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት ዛሬ በራስ ሆቴል በድምቀት እንደሚያከብር የማህበሩ ፕሬዚዳንት ሀኒሳ ሽኩር ገለፁ፡፡   በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ ማህበሩ ያሳለፈው የ10 ዓመት ጉዞ ስኬትና ፈተና የሚወሳ ሲሆን የተለያዩ ግጥሞች፣ወጎችና ሌሎች የኪነ ጥበብ ፕሮግራሞች ለታዳሚ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡   የስነ-ፅሁፍ ባለሙያዎችና የጥበብ ቤተሰቦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ክብረ በዓሉን እንደሚታደሙ ታውቋል፡፡

Read 535 times