Monday, 18 December 2017 13:30

“ኦዳ” የሽልማት ሥነ-ስርዓት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በሻቱ ቶለማሪያም መልቲሚዲያ ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በኦሮምኛ ብቻ የተሰሩ የኪነ-ጥበብ ስራዎችንና ከያኒዎችን የሚሸልምበት “ኦዳ” የኪነ-ጥበብ ሽልማት ለመጀመሪያ ጊዜ አዘጋጀ፡፡ ጥር 5 ቀን 2010 ዓ.ም በኦሮሞ ባህል ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ የሽልማት ሥነስርዓት ላይ በ11 ዘርፎች ሽልማት የሚሰጥ ሲሆን ዘርፎቹም የአመቱ ምርጥ ፊልም፣ ምርጥ ተዋናይ (ተዋናይት)፣ ምርጥ ዳይሬክተር፣ ምርጥ ደራሲ፣ ምርጥ ሲኒማቶግራፈር፣ ምርጥ ቪዲዮ ኤዲተር፣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ፣ ምርጥ የሙዚቃ አልበም፣ ምርጥ ነጠላ ዜማ፣ ምርጥ ቪዲዮ ክሊፕ፣ ምርጥ አቀናባሪና ምርጥ ጀማሪ ድምፃዊ እንደሆኑ በሻቱ ቶለማሪያም መልቲ ሚዲያ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ በ2009 ዓ.ም ብቻ የተሰሩ የኪነ-ጥበብ ስራዎች የሚሸለሙ ሲሆን ሽልማቱ በየዓመቱ በቋሚነት እንደሚቀጥል የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ጋዜጠኛ በሻቱ ቶለማሪያም ለአዲስ አድማስ ገልፃለች፡፡

Read 1615 times