Saturday, 12 May 2018 15:06

“የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ” ቁጥር 2 መፅሐፍ እየተነበበ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(75 votes)

በታሪክ መፅሐፍቶቹ የሚታወቀው ደራሲና ጋዜጠኛ ፍስሃ ያዜ የፃፈው “የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ” ቁጥር 2 መፅሐፍ እየተነበበ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የመፅሐፉ የመጀመርያ ክፍል በአንባቢያን ዘንድ ተወዳጅነትን እንዳገኘ የተገለፀ ሲሆን ቁጥር ሁለቱ፤  ኢትዮጵያ በሌሎች አገራት አይን በምን መልኩ እንደምትታይ፣ አለምን በስልጣኔና በሀብት ከሚዘውሩት “ጂ 20” (ግሩፕ ሃያ) አገራት አንፃር የት እንዳለች እንዲሁም ከገናና ታሪኳ ጋር እያመሳከረ ይተርካል ተብሏል፡፡ በ360 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፣ በ125 ብር ከ50 ሳንቲም እየተሸጠ ነው፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም “የኢትዮጵያ የ5 ሺህ ዘመን ታሪክ ከኖህ እስከ ኢህአዴግ”፣ “እኔ እና ቹ”፣ “ባሪያና ዲያስፖራ” እና “የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ” ቁጥር 1ን ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡

Read 18230 times