የቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ እህት ኩባንያ የሆነው “ብራና አሳታሚ” ያሳተማቸውን ሰባት መፃሕፍት ዛሬ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡ የአሳታሚ ድርጅቱ የአርትኦት ክፍል ሃላፊ አቶ ባየልኝ አያሌው ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት፤ ከመፃሕፍቱ መካከል በሶማሊኛ የተፃፉ የልጆች መፃሕፍት ይገኙበታል፡፡ አድራሻውን ቦሌ ፍላሚንጐ እና ለገሃር አካባቢ በሚገኘው ጐማ ቁጠባ ያደረገው አሳታሚ፤ ዛሬ ከጧቱ ሦስት ሰዓት መፃሕፍቱን በሂልተን ሲያስመርቅ በሕትመት ችግሮችና መፍትሔዎች ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ይታወቃል፡፡