Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 04 August 2012 11:25

የጀምስ ቦንድ 23ኛ ፊልም መተዋወቅ ጀመረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

23ኛው የጀምስ ቦንድ ፊልም “ስካይ ፎልስ”  ሰሞኑን መተዋወቅ ጀምረ፡፡ በተቀነጨበው ትእይንት ቦንድ ሲሞት መታየቱ ትኩረት መሳቡን ቢቢሲ አስታወቀ፡፡ የቦንድ ገፀባህርይ ሲሞት የሚታየው አሳዳጆቹን ለማዘናጋት በተፈጠረ ቅንብር መሆኑን የገለፀው ቢቢሲ፤ በሰላዩ ዘመቻ ከሞት በኋላ ህይወት መኖሩን ለማመልከት የተሰራ እንደሆነ አብራርቷል፡፡ “ስካይ ፎልስ” ከአምስት ወራት በኋላ በመላው አለም እንደሚታይ ይጠበቃል፡፡ በመሪ ተዋናይነት የሰራው ዳንኤል ክሬግ ሲሆን   የኦስካር ተሸላሚው ስፔናዊ ተዋናይ ጃቪዬር ባርደምንና ራልፍ ፊነስን ማሳተፉ ታውቋል፡፡  በ150 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተሰራው ፊልሙ፤  ለ44 ዓመቱ እንግሊዛዊ ተዋናይ ዳንኤል ክሬግ ሶስተኛው የጀምስ ቦንድ ፊልም ይሆናል፡፡

ተዋናዩ በ2006 “ካሲኖ ሮያሌ”ን፣ በ2008 እ.ኤ.አ ደግሞ “ዘ ኳንተም ሶላስ” በተባሉ ፊልሞች አስደናቂ የትወና ብቃት ማሳየቱ ይታወቃል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኤምጂኤም የተባለው ኩባንያ  22 የጀምስ ቦንድ ፊልሞችን  በዲቪዲ ስብስብ አዘጋጅቷል፡፡ የፊልሙን 50ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግም ከአራት ወራት በኋላ   ለዓለም ገበያ እንደሚቀርብም ተነግሯል፡፡  ከ1993 እስከ 2008 እ.ኤ.አ የታዩትን  22ቱ የጀምስ ቦንድ ፊልሞች ላይ ከዳንኤል ክሬግ በፊት ሲንኮነሪን፤ ሮጀር ሙርንና ፒርስ ብሮንስናንን በመሪ ተዋናይነት ሰርተዋል፡፡ ፊልሞቹ በመላው አለም  12.71 ቢሊዮን ዶላር አስገኝተዋል፡፡

 

 

 

Read 1335 times Last modified on Saturday, 04 August 2012 11:29