Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 04 August 2012 12:01

“ኩርቢት” እና “ያልኖሩ ቀኖች” ለንባብ በቁ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 

ራዲሼቭን የሚዘክር የሥነጽሑፍ ምሽት
ሰኞ ይቀርባል
ደራሲና ሃያሲ አለማየሁ ገላጋይ ያዘጋጀው 14 አጫጭር ልቦለዶች የተካተቱበት “ኩርቢት” የአጭር
ልቦለዶች መድበል ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ 127 ገፆች ያሉት መጽሐፍ በ20 ብር እየሸጠ ነው፡፡
አለማየሁ ካሁን ቀደም “አጥቢያ” ፣ “ቅበላ”፣ እና “ስብሃት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት”
በተሰኙ መፃሕፍቱ ይበልጥ ይታወቃል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ በጌድዮን ንጉሤ የተዘጋጁ ግጥሞች
የተካተቱበት “ያልኖሩ ቀኖች” የግጥም መድበል ለንባብ በቃ፡፡ 87 ገፆች ያሉት መጽሐፍ፤ በሐገር
ውስጥ 19.99 ብር በውጭ ሀገራት ደግሞ 14.99 ብር ይሸጣል፡፡
በሌላም በኩል እ.ኤ.አ ከ1749 እስከ 1802 የኖረው የታላቋ ካትሪን ዘመን ሩስያ ዝነኛ ደራሲና ሃያሲ
አሌክሳንደር ኒኮላየቪች ራዲሽየቭ 263ኛ ልደት መታሰቢያ በማስመልከት ወርሃዊ የሥነጽሑፍ ምሽት
ተዘጋጀ፡፡ ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት አዲስ አበባ ፒያሳ በሚገኘው አዳራሹ ያዘጋጀው የሩስያ የሳይንስ እና
የባህል ማዕከል ነው፡፡

 

ራዲሼቭን የሚዘክር የሥነጽሑፍ ምሽት ሰኞ ይቀርባል

ደራሲና ሃያሲ አለማየሁ ገላጋይ ያዘጋጀው 14 አጫጭር ልቦለዶች የተካተቱበት “ኩርቢት” የአጭር ልቦለዶች መድበል ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ 127 ገፆች ያሉት መጽሐፍ በ20 ብር እየሸጠ ነው፡፡አለማየሁ ካሁን ቀደም “አጥቢያ” ፣ “ቅበላ”፣ እና “ስብሃት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት” በተሰኙ መፃሕፍቱ ይበልጥ ይታወቃል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ በጌድዮን ንጉሤ የተዘጋጁ ግጥሞች የተካተቱበት “ያልኖሩ ቀኖች” የግጥም መድበል ለንባብ በቃ፡፡

87 ገፆች ያሉት መጽሐፍ፤ በሐገር ውስጥ 19.99 ብር በውጭ ሀገራት ደግሞ 14.99 ብር ይሸጣል፡፡ በሌላም በኩል እ.ኤ.አ ከ1749 እስከ 1802 የኖረው የታላቋ ካትሪን ዘመን ሩስያ ዝነኛ ደራሲና ሃያሲ አሌክሳንደር ኒኮላየቪች ራዲሽየቭ 263ኛ ልደት መታሰቢያ በማስመልከት ወርሃዊ የሥነጽሑፍ ምሽት ተዘጋጀ፡፡ ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት አዲስ አበባ ፒያሳ በሚገኘው አዳራሹ ያዘጋጀው የሩስያ የሳይንስ እና የባህል ማዕከል ነው፡፡

 

 

 

Read 1367 times