Thursday, 03 December 2020 14:20

ተፈላጊዎቹ የህወኃት አመራሮች ለሁለት ተከፍለዋል ተባለ

Written by 
Rate this item
(13 votes)

;የዐቢይን ጭንቅላት  አልቻልነውም” ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም
መንግስት በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ከሚፈልጋቸውና እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ጥሪ ከቀረበላቸው ከፍተኛ የሕወኃት አመራሮች አንዷ የሆኑት የቀድሞ የፌደሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ከትላንት በስቲያ እጃቸውን በመስጠት የመጀመሪያዋ አመራር ሆነዋል፡፡ በሽሽት ላይ የሚገኘው የህወኃት ከፍተኛ አመራር #እጅ እንስጥ፤አንስጥ; በሚል ለሁለት ተከፍለዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡  
ወ/ሮ ኬሪያ በቪድዮ በተቀረጹትና በቅርቡ ይለቀቃል በተባለው ቪዲዮ፤ የጠ/ሚኒስትር ዐቢይ መንግስት ህወኃትን በጦርነቱ እንዳሸነፈው በግልጽ አምነዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲናገሩ፤ #የዐቢይን ጭንቅላትና ፍጥነት መቋቋም ስላልቻልን ነው; ብለዋል፡፡
“ለነገሩ አሁን አይደለም  የዐቢይን ጭንቅላት መቋቋም ያልቻልነው” ይላሉ ወ/ሮ ኬሪያ፤ “ ከፓርቲያችን ሲያባርረን….. እያንዳንዷን  አጀንዳ ተንትነን ሳናበቃ…. ሌላ አጀንዳ ያሸክመናል…በዚህም .ግራ ገባን” ሲሉም ያስረዳሉ፤ የህወሃት ከፍተኛ አመራሯ፡፡ ፓርቲያቸው የተጋረጠበትን ተግዳሮትም ሲቀጥሉ፡-“ራሳችንን በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ማየት ተሳነን፤በፍጥነቱና በሚነካካቸው በርካታ ጉዳዮች ውስጥ አሰረን፤ከፓርቲያችን ኢህአዴግ አንደፋድፎ አባረረን” ሲሉም ጠ/ሚኒስትሩን እንዳልቻሏቸው ጠቅሰዋል፡፡  
በዐቢይ አጀንዳ ሰጪነት ጦርነቱን እናሸንፋለን ብለን ተሸንፈናል ብለዋል-  ወ/ሮ ኬሪያ፡፡ ”የዶ/ር ዐቢይን ፍጥነቱንና ቴክኖሎጂውን መቋቋም አልቻልንም፤በጦርነቱ ሙሉ በሙሉ እንደተሸነፍን አምነናል”ሲሉም እውነታውን አስረድተዋል፡፡ ወ/ሮ ኬሪያ ያሉት ሁሉ መሬት ላይ የሚታይ ተጨባጭ እውነት ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፤የንግግራቸውን ዓላማ እንደሚጠራጠሩት ግን ይገልጻሉ፤ምክንያታቸውም #ከዚህ ቀደም  ህወሃት ሽንፈትን በግልፅ የማመን ባህል የለውም; የሚል ነው፡፡  

Read 6283 times