Saturday, 26 December 2020 09:49

“የቀድሞ ወረዳችን እንዲመለስልን 25 ዓመት ሙሉ ጮኸናል” የገምዛ ወረዳ ነዋሪ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

           በቀድሞው ይፋትና ጥሙጋ አውራጃ ውስጥ ይገኝ ነበር- ገምዛ ወረዳ፡፡ የወረዳው ዋና ከተማ እድሜም እነ ደብረ ብርሃን ይቀድማል ይላሉ የአካባቢው
 አባቶች። በ1987 ዓ.ም ያልተጠበቀ የጎርፍ አደጋ እስኪከሰት ድረስ ወደ 23 የሚጠጉ ቀበሌዎችን አካትቶ ገምዛ ወረዳ ተብሎ  ነበር የሚጠራው።
አሁንም ምርጫ ቦርድ ምርጫ ሲካሄድ፣ “ለገምዛ ወረዳ ምርጫ ማዕከል” ብሎ እንደሚጠራ  ነዋሪዎች ይናገራሉ በቁጭት፡፡ ከአዲስ አበባ በ300  
ኪ.ሜ ርቀት ላይ  በሰሜን ሸዋ ዞን ስር የሚገኘው ገምዛ፤ ትልቅና ሰንሰለታማ ተራሮችን ተንተርሳ በምትገኘው ማጀቴ ከተማ ማዕከልነት የሚተዳደር
ሲሆን በተፈጥሮ እጅግ የታደለ ውሃ ያለቆጣሪና የሃይል ማጎልበቻ የሚንፎለፎልበት በሽንኩርት፣ በአትክልትና በፍራፍሬ፣ በነጭ ጤፍ ምርት እንዲሁም
በሸንኮራ አገዳ የተትረፈረፈ ምድር ነው፡፡ የታታሪ ህዝብ መፍለቂያ የሆነው ገምዛ፤ ወይናደጋ  የአየር ጠባዩ ህይወት ላለው ፍጡር ሁሉ ተስማሚ ነው፡፡
አንጋፋው ደራሲ፣ ኃይለመለኮት መዋዕል "ጉንጉን" የተሰኘ ልቦለድ መፅሐፍ አማካኝነት ማጀቴን እኔን  ጨምሮ የብዙዎች የህልም ከተማ ናት። ህዝቡ
በስራው በምርቱ በአካባቢው ደስተኛ ቢሆንም ከ25 ዓመት ወዲህ ግን አንድ ህመም የሆነበት ነገር አጋጥሞት እህህ ሲል ከርሟል።የ1987 የገምዛ ወረዳ የችግር መንስኤ
በ1987 ምሽት በአካባቢው ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ዱብዕዳ ገጠመን ይላሉ- የከተማው ተወላጅና ባለሃብት ወ/ሮ ዘነቡ -----። "ሌሊት
ሰው በሰላም በተኛበት "አመዴ ይመር" የተሰኘ ወንዝ ድንገት ገንፍሎ ከተማውን አጥለቀለቀው። በሰላም የተኛው ህዝብ በጎርፍ ተወሰደ። አስክሬኑ
የተገኘው ወደ 60 የሚጠጋ ወገን ስንቀብር፣ በርካታዎች የት እንደገቡ ያልታወቀበት ትልቅ አደጋ ገጠመን" ሲሉ አሳዛኙን ክስተት ያስታውሳሉ።  
አይናቸው እንባ እየቋጠረ።
ይህ ከፍተኛ ድንጋጤና ሀዘን ያስከተለውን ቀውስ ለማረጋጋት፣ ህዝቡ ሲረባረብ፣ ከተማው ከአደጋ እስኪያገግም በሚል የገምዛ ወረዳን ሙሉ ሰነድ
ከማጀቴ ወደ 60 ኪ.ሜ በሚርቅ አንጾኪያ ወደተባለ አካባቢ መኮይ ከተማ አዛወሩት ይላሉ። ማጀቴን አባቴ ነው ያቀናውት የሚሉት ሌላዋ የከተማው
አንጋፋ እናት ወይዘሮ እናኒሁሴን። ህዝቡ ትኩረቱ ሀዘኑ ላይ ስለነበር ከተማው እስኪረጋጋ በሚል ወረዳው ወደ አንጾኪያ መኮይ ከተማ መሄዱን
አልተቃወመም ነበር ብለዋል፡፡
ሀዘኑ ከበረደ ህዝቡ ከተረጋጋና ወደ መደበኛ ህይወት መመለሱን ተከትሎ ወረዳው ወደ ማጀቴ ይመለስ ቢባልም የሚሆን አልሆነም። እነሆ ይሄ ጥያቄ
ድፍን 25 ዓመትቱን  ጨርሶ 26ኛ ዓመቱን እንደጀመረ ነዋሪው በቁጭት ይናገራል። እስከ ክልል ድረስ የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች ፣ የአገር
ሽማግሌዎች፣ ነጋዴዎች፣ አመራሮች እየተመላለሱ ጠየቁ። በዚህ  መሃል አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩበት ጊዜ ቦታው ድረስ
መጥተው፣ የህዝቡን ጥያቄ አድምጠው፣ “ጉዳዩ ይስተካከላል” በሚል ቃል ገብተው መሄዳቸውን የሚጠቅሱት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ሆኖም፤ ምንም ምላሽ
ግን አልተገኘምይላሉ። በቅርቡ ወደ ፌደራል ሃላፊነት የመጡትና በወቅቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ ተመስገን ጥሩነህም በቦታው
ተገኝተው ነበር።
ሆኖም በርካታ አዳዲስ ወረዳዎች ሲዋቀሩ፣ “ነባር ወረዳችን ይመለስልን” ያልነው የገምዛ ወረዳ ህዝቦች፤ ምን በደል ብንሰራ ነው ጥያቄችን የተገፋው
ሲሉ በቅሬታ ይጠይቃሉ። ይህን ጥያቄ  ላለመመለስ ብዙ ዞኑ ሴራ ሰርቶብናል ይላሉ- የማጀቴ ከተማ ነዋሪዎችና አርሶ አደሮች።
ከ23 ቀበሌ አራቱን አንድ ቀበሌ 3ቱን አንድ ቀበሌ፣ እያደረጉ በማጠፍ፣ አሁን ገምዛ ወረዳ 5 ቀበሌ ብቻ እንዲኖራት አደረጉ፤ ትክክለኛና ገለልተኛ
ቆጣሪ ቢመጣ፣ የዚህ ወረዳ ህዝብ ከመቶ ሺህ በላይ ይልቃል። ግን ይህንንም ማመን አልተፈለገም ባይ ናቸው። በማጀቴ ከተማ ውስጥ አምስት
ባንኮች፣ ከ17 በላይ ፎቆች፣ በርካታ መሰረተ ልማቶች የተዘረጉለት በመሪ ማዘጋጃ ቤትነት ደረጃ ያለቸው ማጀቴ፤ በአዲስ አበባ ትልልቅ ሆቴሎችን፣
ህንፃዎችን፣ የንግድ ድርጅቶችን የመሰረቱ ከ1ሺህ በላይ ባለሃብቶችን ያፈራች አገር ብትሆንም፣ እነዚህ ባለሀብቶች  በትውልድ ቀያቸው ማጀቴ ላይ ብዙ
ኢንቨስትመንት ለማፍሰስ አንጾኪያ ወረዳ ድረስ ሄደው ፈቃድ ሲጠይቁ፣ በተለያየ ምክንያት ጥያቄያቸው ውድቅ እየተደረገ ተስፋ በመቁረጥ፣በሌላ ከተማ
ኢንቨስት ለማድረግ ተገድደዋል። በዚህ ምክንያት በገምዛ ወረዳ ህዝብ ላይ ከፍተኛ በደልና መሸማቀቅ ሲደርስ ቆይቷል ብለዋል። ባለፈው ቅዳሜ ወደ
ማጀቴ ለተጓዘው የጋዜጠኞች ቡድን።
ሌላው የገምዛ ወረዳ ህዝብ ጥያቄ
በ2008 ዓ.ም ኦነግ በአካባቢው ላይ በከፈተው ተኩስ በአጣዬና በማጀቴ በርካታ ሰዎች ሲሞቱ ብዙዎች መቁሰላቸውን  የአካባቢው ነዋሪዎች
ይናገራሉ። ወደ የትኛውም ቦታ ለመውጣት እንደነ ጨፋ ሮቢት ያሉ የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ከተማዎችን ማቋረጥ ይጠበቅባቸዋል። በወቅቱም ከኦነግ
ጋር በተፈጠረ ግጭት 19 የማጀቴ ሰዎች በጥይት ተመትተው ህክምና፣ ቢያገኙ ሊተርፉ ሲችሉ፣ መውጫና ወደ ህክምና መድረሻ መንገድ በማጣታቸው
ህይወታቸው ስለማለፉን በሃዘንና በቁጭት  ያስታውሳሉ። “ዙሪያውን በተለያዩ አካባቢዎች የተከበብን፣ ክፉ ቀን ቢመጣ ከመሞት ውጪ ሌላ እጣ የሌለን
የምናሳዝን ህዝቦች ነን” ይላሉ ነዋሪዎቹ።
በዚህም የተነሳ ቀጥታ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደን መንገድ በሚያመቸን በኩል ይሰራልን ብለን ሰሚ አጥተን፣ ይሄው የአንድ ወጣት እድሜ ያህል
ስንጮህ ኖረናል። ለዳኝነት፣ ለልማት ጥያቄ፣ ለማንኛውም ጉዳይ አንጾኪያ ወረዳ መኮይ ከተማ ድረስ መመላለስ ቢታክተ፣ን "መንግስት ምላሽ ካልሰጠን
አንድም አስተዳዳሪ አንቀበልም፤ ራሳችን በራሳችን እንተዳደራለን። አንድም አራት ቁጥር ታርጋ ያለው መኪና ወደ ከተማ እንዳይገባ ብለን ከለከልን፤
ለ11 ወራት ያለ መንግስት" ተዳድረናል። በዚህ 11 ወር ውስጥ የመንግስት አስተዳዳሪም፣ በጀትም ምንም ነገር ከመንግስት ሳንፈልግ በከተማችን
አንድም የፀጥታ ችግር ሳይከሰት ራሳችንን በራሳችን አስተዳድረናል” ይላሉ። በ1987 በጎርፍ ከሞቱት ውስጥ አንዱ የእኔ ልጅ ነው ያሉት አቶ ታጁ
መሃመድ እንገኛለን፡፡”ሆኖም፤ በልማት፣ በአገራዊ ጉዳይ፣ በአባይ ግድብ በቅርቡ በአገር ላይ በተከሰተው ችግር ከመንግስት ጎን ሆነን የሚጠበቅብንን
እያደረግን በቀን ከ150 እስከ 200 መኪና ሽንኩርት፣ አትክልትና ፍራፍሬ በሌለን መንገድ ለአገር ገበያ እያቀረብን ፣ በአመት ሶስት ጊዜ እያመረትን፣
እየታተርን መንግስት ከ20 በላይ አዳዲስ ወረዳዎች ተዋቅረው ሲሰጡ እኛ ነባር ወረዳችንን ገምዛን መጠየቃችን ለምን ሀጢያት ሆነ ሲሉ ጠይቀዋል።
“መንግስት የአካባቢውን ሁኔታ፣ የህዝቡን ቁጥር፣ የከተማውን እድገት የታጠፉ ቀበሌዎችን ወደነበሩበት መልሶ ከጥንት ጀምሮ ወረዳችን የነበረውን
ይመለስልንና በቅርበት እንዳኝ፣ ልማት እንጠይቅ፣ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን እንፈጽም” በማለት የቀድሞ ወረዳቸው እንዲመለስላቸው ጠይቀዋል። በቅርበት
ሆኖ የሚያፅናናቸውና የሚደግፋቸውን የኤፍራታ ግድም ወረዳን ህዝብና አስተዳዳሪዎቹን በእጅጉ አመስግነዋል።

Read 12114 times