ሌላው ታዋቂ የፊልም ዲያሬክተር ስቲቨን ስፒልበርግ ዘንድሮ ለእይታ በበቁለት ‹ዘ አድቬንቸርስ ኦፍ ቲን ቲን› እና ‹ዋር ሆርስ› በተባሉ ፊልሞቹ እንዲሁም ‹ዘ ስማሽ› በተባለ የቴሌቭዥ ቶክ ሾው ባገኘው 130 ሚሊዮን ዶላር 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ የፓይሬትስ ኦፍ ካረቢያን ፊልሞች ዲያሬክተር ጄሪ ብሩክ ሄበር በ115 ሚሊዮን ዶላር ገቢው 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፤ ራፕሩ ዶር ድሬ ‹ቢትስ› በተባለ የጆሮ ማዳመጫ አምራች ኩባንያው አማካኝነት ባገኘው 110 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አምስተኛ ደረጃ መውሰዱን የፎርብስ ሪፖርት አመልክቷል፡፡ በአሜሪካ የቴሌቭዥን ንግስት በሚል የምትታወቅው ኦፕራ ባላት የሃብት መጠን ቀዳሚዋ ጥቁር አሜሪካዊ ስትሆን እስከ 2.7 ቢሊዮን ዶላር እንዳካበተች ይነገርላታል፡፡