ታዋቂው ደራሲ አዳም ረታ ካሁን ቀደም ለብቻው ያሳተማቸው “ማህሌት”፣ “ግራጫ ቃጭሎች”፣ “አለንጋና ምስር”፣ “ከሰማይ የወረደ ፍርፍር” እና “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” የሚሉ መፃሕፍትና ከሌሎች ፀሐፍት ጋር ያዘጋጀው በርካታ መፃሕፍት አሉት፡፡ “የአቤ ቶክቻው ምፀቶች ሽሙጦች 3” በሚል ርእስ በአበበ ቶላ የተዘጋጀው ፖለቲካዊ መፅሐፍ 36 ታሪኮችን የያዘ ሲሆን 175 ገፆች አሉት፡፡ የመፅሐፉ ዋጋ 35 ብር ነው፡፡ በስደት ከሚገኝበት ሃገር መፅሐፉን ያዘጋጀው አበበ ቶላ፤ አንዳንዶቹን ታሪኮች በማህበራዊ ድረገፅ ሲያስነብብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በተያያዘ ዜና በእርቅይሁን በላይነህ የቀረበው “ታዳኤል” የተሰኘ ረዥም ልቦለድ ከትናንት ጀምሮ ለንባብ በቃ፡፡ 256 ገፆች ያሉት መፅሐፍ ብሔራዊ ስሜት ላይ እንደሚያተኩር ደራሲው ገልጿል፡፡ የመፅሐፉ ዋጋ 44 ብር ነው፡፡ በሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድራማዎች ፀሐፊነቱ የሚታወቀው እርቅይሁን፤ ካሁን በፊት “ያልተጠቡ ጡቶች” የተሰኘ የአጭር ልቦለድ መፅሐፍ አሳትሟል፡፡