Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 08 September 2012 13:04

“የኩሽ ምድር” ፊልም ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በሄቨን ኦፍ ኩሽ ፊልም ፕሮዳክሽን የተዘጋጀው “የኩሽ ምድር” ልብ ሰቀላ ድራማ ፊልም ነገ በአዲስ አበባ እና በክልል ሲኒማ ቤቶች እንደሚመረቅ አዘጋጆቹ ገለፁ፡፡ በሌሊሳ አለማየሁ ተፅፎ አርአያ ኪሮስ ያዘጋጀው ፊልም የ100 ደቂቃ ርዝመት ያለው ሲሆን ለመሥራት ሁለት ዓመት ፈጅቷል ተብሏል፡፡ በፊልሙ ላይ ሰሎሞን ሙሄ፣ ህሊና ጌታቸው፣ ትዕግስት አሰፋ፣ አበበ ወርቁ እና ሌሎች ተውነውበታል፡፡ በሌላ በኩል ክሬቲቭ ፊልም ፕሮዳክሽን እና ስልጠና ኃ.የተ.የግ.ማህበር በፊልም ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነገ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡ ተማሪዎቹ ከጧቱ 3 ሰዓት በሩስያ ሳይንስ እና ባህል ማእከል ፑሽኪን አዳራሽ ሲመረቁ በሥልጠናው ሂደት የሠሯቸው ፊልሞችና የዘፈን ትዕይንቶች (ክሊፖች) ለተመራቂዎች ቤተሰቦች እና ሌሎች እንግዶች ይቀርባሉ፡፡

 

 

Read 1286 times Last modified on Saturday, 08 September 2012 13:06