• ማስተማር ሁለቴ እንደ መማር ነው።
ጆሴፍ ጆበርት
• በእውቀት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ምርጡን ወለድ ይከፍላል።
ቤንጃሚን ፍራንክሊን
• የትምህርት አላማ ባዶ አእምሮን በክፍት አእምሮ መተካት ነው።
ማልኮም ፎርብስ
• ትምህርት ስራን ብቻ ማስተማር የለበትም፤ ህይወትንም ጭምር እንጂ፡፡
ደብሊው.ዱ ቦይስ
• መደበኛ ትምህርት መተዳደሪያህን ይሰጥሀል፤ ራስ አገዝ ትምህርት ሀብት ይፈጥርልሀል።
ጂም ሮህን
• የትምህርት ስር መራራ ነው፤ፍሬው ግን ጣፋጭ ነው፡፡
አሪስቶትል
• የትምህርት ቤትን በር የሚከፍት፣ እርሱ፣ የወህኒ ቤትን በር ይዘጋል፡፡
ቪክቶር ሁጉ
• ትምህርት ውድ ከመሰለህ ድንቁርናን ሞክረው፡፡
ኤንዲ ማኪንታየር
• የመማር ፍቅር አዳብር፡፡ ከተሳካልህ መቼም ማደግ አታቆምም፡፡
አንቶኒ ጄ. ዲ’አንጄሎ
• ትምህርት ለህይወት ዝግጅት አይደለም፤ ህይወት ራሱ ነው፡፡
ጆን ድዌይ
• አንድን ሀሳብ ሳያምኑበት ማስተናገድ መቻል የተማረ ሰው መለያ ነው፡፡
አሪስቶትል
• የእውነተኛ ትምህርት የመጨረሻ ውጤት ለውጥ ነው፡፡
ሊዩ ቡስካሊያ
• የትምህርት ግብ፤ ዕውቀትን ማሳደግና እውነትን ማሰራጨት ነው፡፡
ጆን ኤፍ. ኬኔዲ
• ትምህርት የነጻነትን ወርቃማ በር መክፈቻ ቁልፍ ነው፡፡
ጆርጅ ዋሽንግተን ካርቨር
• የዐለም እድገት ሙሉ በሙሉ የተሞረከዘው በትምህርት ላይ ነው፡፡
ጆርጅ ኢስትማን
Published in
ጥበብ