ክራር ኮሌክቲቭ ካለፈው አንድ ወር ወዲህ በአፍሪካን ኤክስፕረስ አማካኝነት በዩናይትድ ኪንግደም ስድስት ከተሞች በተዘጋጁ ኮንሰርቶችና ሌሎች የሙዚቃ ዘግጅቶች ላይ ሲሳተፍ ሰንብቷል፡፡ በአፍሪካን ኤክስፐርስ ቱር ክራር ኮሌክቲቭ ጋር አይማዱክ ማርያም ፋቱማታ ሲያዋራ፣ ቱዋማኒ ዲያቤቴ፣ ቶኒ አለን፣ ኒኮላስጃፒ እና ኪያላላ ግሬጅ ይገኙበታል፡፡
የክራር ኮሌክቲቭን የመጀመሪያ አልበም “ኢትዮጵያ ሱፕር ክራር”ን የገመገመው የጋርዲያን ጋዜጣ ዘገባ ባንዱ የኢትዮጵያ ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችን፣ (ክራርና ከበሮን) በባህላዊ የአዘፋፈን ቅላፄ ውዝዋዜ በማቅረብ በ2012 ዓለም አቀፍ እውቅናቸው ጨምሯል ክራር ኮሌክቲቭ በአልበማቸው እቴሜቴ፣ እንደ እየሩሳሌምና ትዝታ የተባሉት ዘፈኖችንም ይጥላሉ ብሏል፡፡
ክራር ኮሌክቲቭ የሙዚቃ ባንድ ከመመሥረቱ በፊት ኢትዮጵያውያኑ የሙዚቃ ባለሙያዎች በዲያስፖራ ለሚገኙ ማህበረሰቦች የሠርግ ዘፈን በመጫወት ይታወቁ ነበር፡፡ ባንዱ ከተመሠረተ በኋላ ግን በተለያዩ የአውሮፓ አገራት በተካሄዱ የሙዚቃ ፌስቲቫሎች ላይ ዝግጅቶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን በለንደን ኦሎምፒክ ወቅትም ስራዎቻቸውን ያቀረቡት መድረክ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡