Wednesday, 08 June 2022 00:00

የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

•  11 የምሥራቅ አፍሪካ  አገራት ይሳተፉበታል

የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል፣ ከሰኔ 7 እስከ 12 ቀን 2014 ዓ.ም  በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
‹‹ጥበባትና ባህል ለቀጠናዊ ትስስር›› በሚል መሪ ቃል፣ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትብብር የሚያዘጋጁት የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫልን አስመልክቶ ዛሬ  ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
ክቡር አቶ ቀጄላ መርዳሳ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር እንደገለጹት፤  ኢትዮጵያ ፌስቲቫሉን ማዘጋጀት ስታስብ በመሰረታዊነት የቀጠናው ህዝብ እርስ በእርስ እንዲተዋወቅና የህዝቦች መልካም ግንኙነት እንዲጠናከር እድል መፍጠርን ታሳቢ ተደርጎ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ፌስቲቫሉ በሌላ መልኩ  የኢትዮጵያን ገጽታ ከፍ አድርጎ ለማሳየትና የምስራቅ አፍሪካ አገራትን የባህል ግንኙነት ለማጠናከር ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው፤ ፌስቲቫሉ በአሁኑ ወቅት መካሄዱ በተለይ የባህል ዲፕሎማሲ አካል አድርጎ ከመጠቀም አንፃር ጥሩ እድል እንደሆነ ጠቁመው፤ በተለይ አንድ አፍሪካን ለመፍጠር እየተደረጉ ካሉት እንቅስቃሴዎች አንጻር ጥሩ ጅማሮ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
አስራ አንድ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ይተሳተፋሉ ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ፌስቲቫል ላይ ልዩ ልዩ ባህላዊ ክዋኔዎች፣ የሰርከስና የጎዳና ላይ ትርዒቶች፣ ሲምፖዚየም፣ ባህላዊ የምግብና የመጠጥ ዐውደ ርዕይ፣ የፊልም ፌስቲቫል፣ እንዲሁም የሙዚቃና  የኪነ ጥበብ ስራዎች እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡

Read 4389 times