Sunday, 26 June 2022 10:02

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

• ፈጣሪ ድምጽ እንድንሰጥ ቢፈልግ ኖሮ እጩዎችን ያቀርብልን ነበር፡፡
     ጄይ ሌኖ
• በሰው አዕምሮ ላይ የሚካሄድ ማናቸውንም ዓይነት ጭቆና እቃወማለሁ፡፡
    ቶማስ ጄፈርሰን
•  በአሜሪካ ማንም ሰው ፕሬዚዳንት መሆን ይችላል። ያ ነው ችግሩ።
   ጆርጅ ካርሊን
•  አንድን ሰውን ወደ ምክር ቤት ልትመራው ትችላለህ፤ እንዲያስብ ግን ልታደርገው አትችልም፡፡
   ሚልተን በርሌ
•  እርስ በርሱ የተከፋፈለ ቤት መቆም አይችልም።
    አብርሃም ሊንከን
•  መሳሳት ሰውኛ ነው፤  ስህተትን በሌላ ፓርቲ ላይ ማላከክ ፖለቲካ ነው።
   ያልታወቀ ተናጋሪ
•  እጅግ ከሚያስፈልገው በላይ ግብር መሰብሰብ ህጋዊ ዝርፊያ ነው፡፡
    ካልቪን ኩሊጅ
•  የምንኖረው ፖለቲካ ፍልስፍናን በተካበት ዓለም ውስጥ ነው፡፡
    ማርቲን ኤል.ግሮስ
•  እኛ መንግስትን ስንዋሽ ወንጀል ነው፡፡ እነሱ እኛን ሲዋሹን ፖለቲካ ነው፡፡
    ቢል ሙሬይ
• እያንዳንዱ ምርጫ የሚወሰነው ድምጽ ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያው በሚወጡ ሰዎች ነው፡፡
   ላሪ ጄ. ሳባቶ
• ዲሞክራሲ ድምጽ የመስጠት መብት ብቻ ሳይሆን በክብር የመኖር መብትም ነው፡፡
   ናኦሚ ክሌይን
•  የታሪክ ጥናት የጥበብ መጀመሪያ ነው፡፡
    ዣን ቦዲን








Read 1763 times