Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 27 October 2012 10:42

ብሪትኒ ስፒርስ ገንዘብ ታባክናለች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ዝነኛዋ አሜሪካዊት አቀንቃኝ ብሪትኒ ስፒርስ ከአራት ዓመት በፊት ከፈረሰው ትዳሯ ጋር በተገናኘ የደረሰባት የስነልቦና ቀውስ ለከፍተኛ የገንዘብ ብክነት ተጋልጣ እንደነበር ተገለፁ፡፡ ዘንድሮ በኤክስ ፋክተር የቴሌቭዥን ተሰጥኦ ፕሮግራም ላይ በዳኝነት መስራት የጀመረችው ብሪትኒ፤ ለዓመት 15 ሚ.ዶላር ተከፍሏታል ተብሏል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት የድምፃዊቷ ማናጀር ሆኖ ሲሰራ የነበረው ሳሚ ሊፍት የሰራሁበት አልተከፈለኝም በሚል በፍ/ቤት ክስ መስርቶ እየተከራከረ ሲሆን የብሪትኒ ቤተሰቦች በበኩላቸው ግለሰቡ ልጃቸውን የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኛ አድርጐብናል ሲሉ ለፍ/ቤቱ አመልክተዋል፡፡

ድምፃዊቷ ከሁለት ዓመት በፊት በአንድ ዓመት ወጪ ያደረገችው ገንዘብ ሰሞኑን ለፍ/ቤት መቅረቡን የዘገበው “ኦኬ” የተባለ ለፀጉሯ 2600 ዶላር፤ ለማሳጅ 4500 ዶላር እንዲሁም ለአልባሳት ከ54ሺ ዶላር በላይ ማውጣቷን አመልክቷል፡፡ ለላውንደሪ፤ ለቤት እንስሶቿ እንክብካቤ፤ ለአስቤዛ እና የተለያዩ ጉዞዎች ወጪ ያደረገችው ደግሞ 180ሺ ዶላር ይጠጋል፡፡ ከመኪናዎቿ ጋር ለተገናኙ ወጪዎች 60ሺ ዶላር አጥፍታለች ተብሏል፡፡ 
የ30 ዓመቷ ብሪትኒ ስፒርስ፤ ባለፉት 12 ወራት በተለያዩ ሥራዎች ከ58 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተከፈላት ሲሆን ከሆሊዉድ ከፍተኛ ተከፋይ ሴቶች በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ፎርብስ መጽሔት አስታውቋል፡፡ አጠቃላይ የሀብቷ መጠን 200 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል፡፡
ባለፉት አስር ዓመታት ሰባት አልበሞችን ያወጣችው ብሪትኒ ስፒርስ፤ በመላው ዓለም ከ100 ሚሊዮን በላይ የአልበሞቿን ቅጂዎች ቸብችባለች፡፡ የግራሚ አዋርድን ጨምሮ ለስድስት የኤምቲቪ የሙዚቃ ቪዲዮ አዋርድ፤ ዘጠኝ የቢልቦርድ የሙዚቃ አዋርድ ሰብስባለች፡፡

Read 1447 times