Saturday, 17 June 2023 00:00

Mama Birth----የእናቶች መውለድ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 በእርግዝና ወቅት በተለይም ለመውለድ በሚቀርቡበት ወቅት በተፈጥሮ መንገድ ለመውለድ የማያስችሉ የተለያዩ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ምንም እንኩዋን ካለምም ችግር አስቀድ ሞውኑ በምጥ አልወልድም፤ የምወልደው በቀዶ ሕክምና ነው ብሎ መወሰን ትክክል ባይሆንም በድንገት ለሚገጥሙ ችግሮች ግን በቀዶ ሕክምናው ለምትወልደውም ይሁን ለሚወለደው ጨቅላ መፍትሔ እንደሚሆን እሙን ነው፡፡
‹‹….በቀዶ ሕክምና አገልግሎት ልጅን ማዋለድ ትንሽ ከበድ ያለ አካሄድ አለው፡፡ ውጫዊ የሰ ውነት አካል በቀጥታ ተቀዶ ልጅን ማግኘት አይቻልም፡፡ በደረጃ ከላይኛው ወደታ ችኛው… አሁንም ወደታችኛው…..አሁንም ወደታችኛው አካል እየሰነጠቁ በጥበብ በመጉዋዝ ልጁ ካለበት ማህጸን ይደረሳል፡፡ ምንጊዜም ወደውስጥ በተመጣ ቁጥር አደጋው ከፍ ያለ ስለ ሚሆን ልምምድ ይፈልጋል፡፡ በከፍተኛ ሐኪሞች ቁጥጥርና ክትትል እንጂ ተለማማጁ በቀጥታ የሚሰራው አይደለም፡፡ ስለዚህም አንድ የህክምና ተማሪ በቀጥታ ወደ ሰው ሰውነት ሄዶ የቀዶ ሕክምናውን ልምምድ ማድረግ ስለማይችል አስቀድሞ የተለያዩ ሞዴሎችን መለማ መድ ይጠበቅበታል፡፡ ይህ ማማ በርዝ የተሰኘው ሰርቶ ማሳያ ለአዋላጅ ሐኪሞች ጥሩ ሰርቶ ማሳያ ነው የሚል እምነት አለ….››
ምንጭ---ዶ/ር ብሩክ ጋሻው በዛ፡፡
የጽንስና ማህጸን ህክምና ተማሪዎች ለወላዶች የቀዶ ህክምና አገልግሎት ለመስጠት በሚሰለጥኑበት ጊዜ በቀጥታ ወደ ሰው ሰውነት እንዲያልፉ አይደረግም፡፡  በመጀመሪያ በከብቶች የውስጥ አካላት እንደልብ፤ጉበት፤ምላስ በመሳሰሉት ላይ ከተለማመዱ በሁዋላ የሰው አካልን በቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ይጀምራሉ፡፡ ማንኛውም ባለሙያ ትምህርቱን ጨርሶ ወደስራ ከመሰማራቱ በፊት እንደየሙያው አይነት ትምህርታዊ ልምምድ ማድረግ የበለጠ በእውቀት እንደሚያንጸው የታወቀ ነው፡፡ የህክምና ባለሙያዎችም ከዚህ ጋር በተያያዘ መንገድ የተለያዩ ትምህርታዊ ልምምዶችን የሚያደር ጉባቸው መሳሪያዎች ቢኖሩአቸው ትምህርቱን ከጨረሱ በሁዋላ በቀጥታ የሚሰማሩበትን ሰዎችን የማዳን ስራ በተገቢው ሁኔታ ይፈጽሙታል የሚል እምነት በመኖሩም በአሁኑ ወቅት ማማ በርዝ የተባለችው የህክምና መለማመጃ ወደ አገር ውስጥ ገብታ በተወሰኑ ሆስፒታሎች ለማለማመጃነት ስራ ላይ እየዋለች ትገኛለች፡፡
ማማበርዝ የምትባለው ሰርቶ ማሳያ የተሰራችው ላርደል በሚባል መቀመጫውን በኖርዌይ ባደረገ ድርጅት ነው፡፡ ከአሁን ቀደም ነሐሴ 24/2013 ዓም በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒ ታል ተካሂዶ በነበረ አውደ ጥናት ተገልጾ የነበረውን እና በጊዜው የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ራሔል ደምሰው እንደገተናገሩት  እስከአሁን ድረስ ብዙ የቀዶ ሕክ ምና አገልግሎት ስልጠና በኢትዮጵያ ወይንም በአፍሪካ በመሰልጠኛ መሳሪያዎች የታገዘ አይደለም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ የልምምድ መሳሪያዎቹ ለአቅ ምም ፈታኝ ስለሆኑ ነው፡፡ በሕክምና ወደ ታካሚዎ ቻችን ከመሄዳችን በፊት መጀመሪያ ስልጠናዎች ይደረጋሉ፡፡ ሰልጣኙ በስልጠና መሳሪያው ላይ እጁን ፈትቶ በደንብ ተለማምዶና በከፍተኛ ሐኪም እየተረዳ አተገባበሩን በደንብ ሲያ ውቅ ከዚያ በሁዋላ እራሱን ችሎ ቀዶ ሕክምና እንዲያደርግ ይፈቀዳል፡፡ ስለዚህ ማንኛው ንም የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ልምምድ የሚያደርግ ሐኪም በመሳሪያዎች ታግዞ ይህንን ቅድመ ዝግጅት ማሟላት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
ከአሁን ቀደም ለስልጠና የበቃቸው ማማ በርዝ እናቶች ከቀዶ ሕክምና ውጭ በተፈጥሮአዊ መንገድ ሲወልዱ በጤናማ ሁኔታ እንዲወልዱና የጨቅላ ሕጻናቶቻቸውም ጤንነት እንዲ ሁም ሕይወት በማይጎዳበት መልኩ እንዲሆን ለማስቻል አዋላጅ ነርሶችን ጨምሮ የህክምና ባለሙያዎችም ስልጠናውን ወስደው ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ ስልጠና ላይ የዋለችው ማማ በርዝ እናቶች በእርግዝና ወቅት የሚኖራቸውን ገጽታ የያዘች እንዲሁም የሚወለደው ጨቅላም አብሮ ያለ ሲሆን ማንኛውም ሰልጣኝ በምን መልኩ ማዋለድን ተግባራዊ እንደሚያደርግ የተመለከቱበት ሁኔታ ነበር፡፡
ማማ በርዝ አሁንም በድጋሚ ከአራት ሆስፒታሎች ማለትም ከወላይታ ሶዶ፤ባህርዳር፤ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ እና ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ባለሙያዎች ለስልጠና ቀርባ ነበር፡፡ እነዚህኞቹ ሐኪሞች ወላዶችን በቀዶ ሕክምና የሚያ ዋልዱ ሲሆኑ ማማ በርዝ የህክምና ተማሪዎችን ለቀዶ ህክምና አገልግሎት አሰልጥኖ ለማዘጋጀት እንዴት እንደምትረዳ አይተዋል፡፡ ይህችኛዋ ማማ በርዝ ቀድሞ ለስልጠና ከቀረበችው ማማ በርዝ ጋር ምንም ልዩነት የላትም፡፡ ልዩነቱ ተግባሩን እውን ማድረጉ ላይ ብቻ ነው፡፡ ቀደም ሲል የነበረው ስልጠና ከቀዶ ሕክምና ውጭ ለሚያዋልዱ ሲሆን ይኼኛው ደግሞ በቀዶ ሕክምና ለሚያዋልዱ ሐኪሞች መቅረቡ ብቻ ነው፡፡ ከአሁን ቀደም ያነጋገርናቸው ወ/ሮ አለምነሽ ተክለ ብርሀን  ከኖርዌይ ላርደን የሚከተለውን መረጃ ሰጥተውን ነበር፡፡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአለም አቀፍ ደረጃ 35% የሚሆኑት ሴቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ ምናልባትም የቀዶ ሕክምና ድጋፍ ሊያስፈ ልጋቸው ይችላል ተብሎ ይገመታል፡፡ ያንን መነሻ በማድረግም የአለም የጤና ድርጅት የአንዲትን ሀገር የተሟላ እርግዝናና የወሊድ አገልግሎት አለ ለማለት ያስችላሉ ተብለው የተቀመጡ ደረጃዎች ወይንም መለኪያዎች አሉት፡፡ ከእነዚህም አንዱ የኦፕራሲዮን ወይንም የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ከ15-25 % በሚሆን ደረጃ ይሰጣል ከተባለ እንደ አንድ ጥሩ የአገል ግሎት ተደራሽነት ይቆጠራል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሚታየው ሁለት የማይገናኙ ወይንም በተለያዩ ጠርዞች ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡ እነርሱም …Too early--------Too late እጅግ በጣም በፍጥነት ወይንም ደግሞ እያስፈለጋቸው በመዘግየት እና Too -much------- Too small ለማያስፈልጋቸውም ለብዙ ሰዎች ወይንም ደግሞ ለሚያስፈል ጋቸውም ሰዎች እንኩዋን ያለመዳረስ በሚል ይከፈላል፡፡
ከላይ የተጠቀሰው ችግር በመላው አለም በብዙ ሀገራት የሚታይ ችግር ሲሆን ምናልባትም በሀገር ደረጃ የሚታይበት ሁኔታም ይበልጥ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ ኢትዮጵያ እንደምሳሌ ስትጠቀስ በገጠርና በከተማው ያለው ሁኔታ የተለያየ ነው ፡፡
እንደሀገር ስሌቱ ሲሰራ ከ80% በላይ ነዋሪው በገጠር የሚገኝ ስለሆነ በዚያ መንገድ ሲታይ የኦፕራሲዮን አገልግሎት የሚ ያገኘው ሰው ብዛት ከ3-5% በላይ አይደለም፡፡ ይህ በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ የሚያሳየው የአገልግሎቱን ተደራሽ አለመሆን ነው፡፡ በአንጻሩ በአዲስ አበባ እና ሌሎች ትላ ልቅ ከተሞች ያለው አገልግሎት ሲታይ ከ40-50% የቀዶ ህክምና አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ምናልባትም በቅርብ ጊዜ የተደረገ ጥናት በእጃችን ባይገኝም ቀደም ሲል የነበረ ጥናት እንደሚገልጸው ጥሩ ኑሮ የሚኖሩ ሰዎች የኑሮ ደረጃና የሀብት መገለጫ ወይንም ደግሞ የተማሩ ሴቶች አገልግሎቱን በስፋት ለመጠቀም ቅርብ ሆነው የሚታዩበት ነገር ስላለ በከተሞች አካባቢ ሰፋ ብሎ ይታያል ፡፡
ምንጭ-፡ወ/ሮ አለምነሽ ተክለ ብርሀን ከላርደን
ግንቦት 18 እና 19/2015 በአዲስ አበባ የማማ በርዝ ስልጠና በተሰጠበት ወቅት የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ራሔል ደምሰው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስትና የፕሮጀክቱ ምክትል ስራ አስኪያጁ ዶ/ር አሸብር ጌታቸው የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት ለአምዱ የማሰልጠና ናሙናዋን መተመለከተ አጠር ያለ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር፡፡
እንደ ዶ/ር ራሔል ከአሁን ቀደም ለስልጠና ቀርባ የነበረችውም የአሁኑዋም ማማ በርዝ ልዩነት የሌላቸው ሲሆን ቀድሞ በተሰጠው ስልጠና መሰረት በተወሰኑ አካባቢዎች ተማሪ ዎችን ለማሰልጠን በተግባር ላይ ውላለች፡፡ ቀደም ሲል ተነድፎ የነበረው ፕሮጀክት ተጠናቆ የማሳያ መሳሪያዋም በሐኪሞች ፤በአዋላጆች እጅ ስልጠና ላይ እየዋለች ሲሆን የሄኛው ፕሮጀክት ደግሞ የቀዶ ሕክምናን ለማድረግና በቀዶ ሕክምና ወቅት ሊገጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት እንዲያስችል ማሳያ ወይንም ማለማመጃ ናት፡፡ በእርግጥ በውጭው አለም የሰው ሰውነት እና አቋም ያላቸው የተለያዩ ደረጃዎችን የያዙ የህክምና መማሪያ ናሙናዎች ቢኖሩም ወደሐገር ውስጥ ገና አልገቡም፡፡ ስለሆነም አሁን እጃችን ላይ ባለው መሳሪያ በሚገባ ካለማመድንና ናሙናዋን ካቀረብን በወደፊቱ አሰራር ለተገልጋዮች ጠቃሚ ይሆናል የሚል እምነት አለን ብለዋል፡፡
ዶ/ር አሸብር እንዳሉት ለስልጠናው የተመረጡት አራት ዩኒቨርሲቲዎች ከሚያስተምሩአቸው ተማሪዎች አንጻር የተመረጡ ሲሆን ከዚህ የሚገኘው እውቀት ለብዙዎች ይዳረሳል የሚል እምነት አለ፡፡ዶ/ር አሸብር እንዳሉት የፕሮጀክቱ መነሻ ወላድ እናቶችንና ጨቅላዎቻቸውን ከጉዳት ለመጠበቅ ብቃት ያለው የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት ማፍራት እንዲሁም  የቀዶ ሕክምናው አገልግሎት በሁሉም ቦታ በተገቢው እንዲሰጥ ለማስቻል ስለሆነ ይህ ይሳካል ብለን እናምናለን ብለዋል፡፡

Read 616 times