Saturday, 17 June 2023 00:00

“ህልማችንና ልባችንን ለህፃናት” የኪነጥበብ ፊስቲቫል ዛሬ ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይንመንት የዘንድሮውን የአፍሪካ የህጻናት ቀን ምክንያት በማድረግ 4 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት “ህልማችንና ልባችንን ለህፃናት” በሚል መሪ ቃል፣ ዛሬ ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00-10፡00 የሚዘልቅ ልዩ ልዩ ኪነ-ጥባባዊ መሰናዶ (ፌስቲቫል) በሀገር ፍቅር ቴአትር ያካሂዳል፡፡
በእለቱም የህፃናት መፃህፍት አውደ ርዕይ፣ እያዝናኑ የሚያስተምሩ የህፃናት ጨዎታዎች፣ ሰርከስ፣ ግጥም፣ ህብረ ዝማሬና ሌሎች ኪነጥበባዊ መሰናዶዎች እንደሚቀርቡ የሰምና ወርቅ መስራችና የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ዓለሙ ገልጿል፡፡
ተሰጥኦ ያላቸው ህፃናት መድረኩን ያደምቁታል ተብሎ በሚጠበቅበት በዚህ ፌስቲቫል፤ ተባባሪ ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ፣ አሉላ ሪቻርድ ፓንክረስት (ዶ/ር)፣ የክብር ዶ/ር ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ፣ ደራሲ፣ መምህርና ሀያሲ ሀይመለኮት መዋእል፣ አርቲስት አዜብ ወርቁና ሌሎም ታዋቂ ግለሰቦች ይገኛሉ ያለው አዘጋጁ፤ መርሃ ግብሩ የክብር አጋር የሆነው “ኪድስ ኬር” አመስግኖ፤ ሁሉም በዚህ ድንቅ መርሃ ግብር ላይ በነፃ እንዲታደም ጋብዟል፡፡


Read 791 times