Saturday, 29 July 2023 12:13

August 1-7 የአለም የጡት ማጥባት ሳምንት

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 ጡት ማጥባትን እንደ አንድ መተኪያ የሌለው ስራ እንመልከተው፡፡
በአለም ላይ ወደ ግማሽ ቢሊዮን የሚሆኑ በስራ ላይ ያሉ እናቶች በአገራቸው ብሔራዊ ደረጃ አስፈላጊው የእናትነት እንክብካቤ አይደረግላቸውም፡፡ወይም መብት አይሰጣቸውም፡፡
በአለም ላይ ወደ 20 ከመቶ የሚሆኑት ሀገራት ቀጣሪዎቹ ለተቀጣሪዎች በእናትነት ወቅት ጡት እንዲያጠቡ ክፍያቸው ሳይቋረጥ እረፍት እና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች እንዳይጉዋደልባቸው እንዲያደርጉ ለስራ ቀጣሪዎች ትእዛዝ ይሰጣሉ፡፡
በአለም ላይ ከሚወለዱት ከግማሽ በታች የሆኑት ጨቅላ ሕጻናት በትክክል እስከ ስድስት ወር እድሜአቸው ድረስ የእናት ጡት ወተት ብቻ ይመገባሉ፡፡
ምንጭ WHO
በየአመቱ በውጭው አቆጣጠር August 1-7 በአለም የጡት ማጥባት ሳምንት ተብሎ ይታሰ ባል፡፡ የእናትን ጡት ማጥባት የልጆችን ጤናና ደህንነት በመጠበቅ ረገድ አንዱና ዋናው መን ገድ ተደርጎ ይታመናል፡፡ እንደ የአለም የጤና ድርጅት ምስክርነትም በአለም ላይ ከሚወለዱ ከግማሽ በታች የሆኑ ጨቅላዎች በትክክል እስከ ስድስት ወር እድሜአቸው ድረስ የእናትን ጡት ወተት የሚመገቡ መሆኑ እርግጥ ነው፡፡
ዶ/ር ፍላጎት ታደሰ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት የዚህ እትም እንግዳ ናቸው፡፡ ዶ/ር ፍላጎት በእርግዝና ጊዜ የጤና ችግር ያለባቸውን እናቶች ህክምና በሚመለከትም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ትምህርት በመከታተል ላይ ናቸው። ዩኒሴፍ፤ የአለም የጤና ድርጅትና ዶ/ር ፍላጎት የሰጡንን መረጃ በማዛመድ ለንባብ ብለነዋል፡፡ የእናት ጡት ወተት ለጨቅላዎች ምንም መተኪያ የሌለው ምርጥ ምግብ ነው፡፡የእናት ጡት ወተት ንጽህናው እና ደህንነቱ የተጠበቀ የበሽታ መከላከያን በውስጡ የያዘ በመሆኑም በህጻንነት ጊዜ የሚታዩ የተለያዩ ህመሞችን የሚከላከል ነው፡፡
የእናት ጡት ወተት ለጨቅላዎቹ የመጀመሪያ እድሜ ቆይታቸው የተመጣጠነ ምግብ በመሆን አቅማቸውን ያጎለብትላቸዋል፡፡ ከዚያም በሚቀጥለው ስድስት ወር እድሜአቸው ግማሽ ያህሉን ወይንም ከዚያ በላይ ለሚሆኑት ከሌሎች ምግቦች ጋር በመቀላቀል እንደተጨማሪ ምግብ ሊቆ ጠር ይችላል፡፡ ጨቅላ ህጻናቱ የእናትን ጡት ወተት እስከ ሁለት አመት ድረስ ቢመገቡም ሊጠ ቀሙ ይችላሉ፡፡        
የእናት ጡት ወተት የተመገቡ ህጻናት የእውቀት ደረጃቸው የተሻለ ሆነው ተገኝተዋል። ክብደትን በሚመለከት ብዙ ጊዜ የተመጣጠነ ክብደት ያላቸው ናቸው፡፡ በሁዋለኛው ዘመናቸው ለስኩዋር በሽታ የመጋለጥ እድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡
ጡት ያጠባች እናት ለጡት እና ለማህጸን ካንሰር የመጋለጥ እድልዋ እጅግ ዝቅተኛ ነው። በአለም ላይ የእናትን ጡት ወተት ይተካሉ የተባሉ የእንዱስትሪ ውጤቶች ያላቸው የዋጋ ንረት በራሱ በቀላሉ ቀላል የማይባል ሲሆን የእናት ጡት ወተት ግን ምንም ዋጋ ሳያስከፍል ፤የተለየ ዝግጅት ሳይደረግለት በቀላሉ ለልጁ ምነጊዜም ቅርብ የሆነ ምግብ ነው፡፡ ከእናትየው የሚገኘውን የተሟላ ምግበ ለጨቅላዎች በመመገብ ብቁ ዜጋን የማፍራት ሂደትን የሚያበረታታ ነው፡፡
ዋና ዋና ነጥቦች፡፡
በአለም ላይ ሁሉም ጨቅላዎችና  ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ የማግኘት መብት አላቸው። በህጻናት መብት ድንጋጌ የሰፈረ መብታቸውም ነው፡፡
በአለም ላይ ያልተመጣጠን ምግብ 45% ለሚሆኑ ህጻናት ሞት ምክንያት ነው፡፡
በአለም ላይ በ2020 እንደተመዘገበው የተመጣጠነ ምግብ ካለማግኘት የተነሳ ከአምስት አመት በታች የሆኑ 149/ ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት በእድሜአቸው ልክ ያላደጉ ፤ ወደ 45 ሚሊዮን የሚሆኑት በሰውነታቸው እንደ እድሜአቸው ሳያድጉ እጅግ የቀጨጩ ሲሆን ወደ 38.9 ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት ደግሞ ከክብደት በላይ ሆነዋል፡፡
በአለም ላይ ወደ 44%የሚሆኑ ጨቅላዎች ማለትም እድሜአቸው ከ0-6 ወር የሚሆናቸው ካለምንም ድብልቅ የእናት ጡት ወተት መመገባቸው ተረጋግጦአል፡፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአለም ላይ ጥቂት ህጻናት ከስድስት ወር በሁዋላ የተሟላ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ ፤ጊዜውን የጠበቀ፤ተጨማሪ ምግብ የሚያገኙ ሲሆን በብዙ ሀገራት ካሉ ህጻናት መካከል ከአንድ አራተኛ በታች የሚሆኑት ማለትም እድሜአቸው ከ6-23 ወራት የሚ ቆጠር ጨቅላዎች ለእድሜአቸው በሚመጥን መንገድ የተመጣጠነ እና ጊዜውን በጠበቀ መልኩ እንደሚመገቡ ይመሰክራሉ፡፡
በአለም ላይ ከ820‚000 በላይ የሚሆኑ ህጻናት ህይወታቸው ሊተርፍ የሚችለው በየአመቱ ከአምስት አመት በታች ያሉት በተለይም ከ0-23 ወራት ድረስ ባለው ጊዜ የእናት ጡት ወተት በተገቢው ያገኙና ተጨማሪ ምግብ በሚያስፈልጋቸው ጊዜም በተገቢው ከተመገቡ ነው፡፡
የእናት ጡት ወተት የሰዎችን የአስተሳሰብ ብልጽግና ፤ደህንነት መሟላት ዋስትና ይሰጣል። በትምህርት ቤታቸው በተገቢው መንገድ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እና ውጤታማ እንዲሆኑ ይረዳል፡፡ በወደፊት ህይወታቸውም ጥሩ ገቢ ያላቸው እና ተፎካካሪ እንዲሆኑ ያግዛል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ የልጆችን ልማት ለማሻሻል እና በጤናቸው ጉድለት ምክንያት ለሚመጡ የጤና ችግሮች የሚመደቡ የኢኮኖሚ ወጪዎችን ለመግታት እንዲሁም በሀገር ደረጃ ለሚከሰቱ የጤና አጠባበቅ ስርአት ሸክምን ለማቃለል እንዲያስችል አስቀድሞውኑ ጨቅላ ህጻናትን የእናት ጡት ወተት ማጥባት ጠቃሚ ይሆናል፡፡
ያልተመጣጠነ ምግብ በአለም ላይ ወደ 2.7 ሚሊዮን ለሚሆኑ ህጻናት ሞት ምክንያት ሲሆን በየአመቱ 45% የሚሆኑ ሞቶች ይመዘገባሉ። ጨቅላዎችና ህጻናቱ ባሉበት እድሜ ያለውን አመጋገብን በተመለከተ ብዙ መሻሻል ያለባቸው ነገሮች መኖራቸው እሙን ነው፡፡ በተለይም የመጀመሪያ ዎቹ 2 አመታት የህጸናት ሕይወት እጅግ አስፈላጊ ጊዜዎች ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ የሚደረግላቸው የእናት ጡት ወተትን የመመገብ እና የተሟላ ምግብ እንዲያገኙ የማድረግ ሂደት ህጻናቱ በከፋ ደረጃ እንዳይታመሙ እና በተሻለ ሁኔታ እንዲያድጉ በአእምሮአቸወም የበለጸጉ እንዲሆኑ ይረዳል፡፡
ስለዚህ የእናት ጡት ወተትን በሚገባ ለህጻናቱ መስጠት በአለማችን በየአመቱ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ወደ 820‚000 ህጻናት እንዳይሞቱ ይረዳል፡፡   
የአለም የጤና ድርጅትና ዩኒሴፍ የሚከተለውን መልእክት ያስተላልፋሉ፡፡
ጨቅላ ህጻናት ገና እንደተወለዱ በአንድ ሰአት ጊዜ ውስጥ የእናት ጡት ወተትን መመገብ መጀመር አለባቸው፡፡
የተወለዱ ጨቅላ ህጻናት እስከ ስድስት ወር እድሜአቸው ድረስ ምንም ሳይቀላቀል የእናት ጡት ወተት ብቻ ሊመገቡ ይገባል፡፡
ጨቅላ ህጻናት እድሜአቸው ስድስት ወር ከሞላ በሁዋላ እስከ 2 አመታቸው ወይንም ከዚያ በሁዋላም ድረስ ከእናት ጡት ወተት በተጨማሪ የተመጣጠነ ምግብ እንዲወስዱ ያስፈልጋል፡፡
እውነታው ከላይ የተገለጸው ቢሆንም በአለም ላይ በርካታ ጨቅላ ህጻናት በትክክል የእናት ጡት ወተት እየተሰጣቸው አለመሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እንደምስክር የሚሆነውም እንደ ውጭው አቆጣጠር ከ2015-2020 ድረስ በአለማችን ላይ ወደ 44% የሚሆኑ ብቻ እድሜአቸው ከ0-6 ወራት የሚሆኑ በትክክል የእናት ጡት ወተት መመገባቸው ተረጋግጦአል፡፡
የእናት ጡት ወተትን ለጨቅላዎች ካለምንም ምግብ ቅልቅል መስጠት ኤችአይቪ ቫይረስ በደ ማቸው ላለባቸው እናቶችም ይመከራል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በመወሰድ ላይ ያለው (ART) ፀረ ኤች አይቪ መድሀኒት እንዲሁም ለህጻናቱ የሚሰጠው የመከላከያ ሲሮፕ (በአፍ የሚወሰድ መድ ሀኒት) መከላከያ ስለሆነ ህጻናቱ እስከ ስድስት ወር እድሜአቸው የእናት ጡት ወተት ብቻ እንዲወስዱ መንገድ ከፍቶአል፡፡ (ART) ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ አደጋውን ይቀንሳል። ከዚያም በሁዋላ ቢያንስ ቢያንስ 12/ወራት እስኪሆናቸው ድረስ የእናት ጡት ወተትን ከተጨ ማሪ ምግቦች ጋር መስጠት ያስፈልጋል፡፡  

Read 627 times