Saturday, 05 August 2023 12:24

ሸራተን አዲስና “ይሳቃል ኢንተርቴይንመንት” ለአዲስ ዓመት ዋዜማ ኮንሰርት ያዘጋጃሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአዲስ ዓመት ዋዜማ ታዋቂ ዓለም አቀፍ አርቲስቶችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት የሙዚቃ አፍቃሪያንን በማዝናናት የሚታወቀው ሸራተን አዲስ ሆቴልና የኢትዮጵያን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም ለማስተዋወቅ የሚተጋው “ይሳቃል ኢንተርቴይመንት” በመተባበር በአዲስ ዓመት ዋዜማ ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚያዘጋጁ ገለፁ።
አዘጋጆቹ ይህን የገለጹት ትላንት ሀምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ረፋድ ላይ በሸራተን አዲስ ሆቴል በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። በዚህ ኮንሰርት ላይ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች አድናቆትና ተቀባይነት ያገኘውና በመድረክ ስሙ “ሬማ” በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ናይጄሪያዊው የአፍሮቢት ስልት አቀንቃኝ ሥራውን የሚያቀርብ ሲሆን፤ በአዲስ የሂፕ ሆፕ ስልት ሙዚቃው ተወዳጅነትን ያተረፈው ልጅ ሚካኤል (ፋፍ)፣ ተወዳጇ ድምፃዊት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲጂ)፣ እንዲሁም ተቀባይትን እያገኙ ከመጡት አዳዲስ ድምፃዊያን አንዱ የሆነው ድምፃዊያን አዲስ ለገሰ ሥራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
የመግቢያ ዋጋንና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ጊዜው ቀረብ ሲል እንደሚያሳውቁም ተጠቁሟል።


Read 1745 times