Wednesday, 09 August 2023 00:00

“የአማርኛ ጥበበ ቃላት ቅኝት” ዛሬ በሀገር ፍቅር አዳራሽ ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በአንጋፋው ደራሲ ሃያሲና የኢኮኖሚ ባለሙያ አስፋው ዳምጤ የተሰናዳው “የአማረኛ ጥበበ ቃላት ቅኝት” የተሰኘ መፅሐፍ፣ ዛሬ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ ይመረቃል፡፡
መፅሐፉ፤ የዘመናት ታሪክን የሚያሳይ፤ የመቶ ዓመት የልብወለድ ታሪኮችን የሚተነትን  ነው ተብሏል፡፡
በምርቃት ሥነስርዓቱ ላይ ሰዓሊ እሸቱ ጥሩነህ፣ ደራሲና መምህር ደረጀ ገብሬ፣ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ፣ ደራሲ ዘነበ ወላ፣ ደራሲና ሰዓሊ ዳንኤል ታዬ፣ ደራሲና አርታኢ ሁሴን ከድር እንዲሁም ኤርሚያስ ሁሴን ጥበባዊ ሥራዎቻቸውን ለታዳሚ የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ይታገሱ ጌትነት ደግሞ መድረኩን ይመራዋል ተብሏል፡፡

Read 1858 times