Saturday, 19 August 2023 20:18

ለኢትዮጵያ ቡድን በባህልና ስፖርት ሚኒስትር በተዘጋጀው “ጀግኖች ለጀግኖች” የሽኝት ፕሮግራም

Written by  ግሩም ሰይፉ
Rate this item
(1 Vote)

“ከእኛ ወርቃማ አትሌቶች ታሪክን ስለተረከባችሁ አልማዞች ናችሁ።”
“ዓላማችሁን አስረዝሙ፥ ኢትዮጵያን አስቀድሙ።”
ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴረሽን ፕሬዝዳንት
“ኢትዮጵያ በ96 ሜዳሊያዎች ከዓለም 7ኛ ደረጃ ላይ ናት”
“ጀግኖች ለአገራቸው ባንዲራ ቅድሚያ ሰጥተው ነው... “መንግስት አትሌቶቻችን እጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲሄዱ ይፈልጋል”
አምባሳደር መሥፍን ቸርነት
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ
“አገራችን ሰላም ከሆነች ልጆቻችን ድል ያደርጋሉ፤ ከተጋገዛችሁ ከተደጋገፋችሁ ... ኢትዮጵያ አገራችን በድል ትመለሳለች።”
አትሌት ብርሐኔ አደሬ
የኦሎምፒክ ኮሚቴ ተቀዳሚ ምክትል  ፕሬዘደንት
“ሩጫ የግል ነው፤ በሀሳብ ስትደጋገፉ ከጎን ላለው ሞራል ነው። ተያይዘው ከሄዱ ማሸነፍ ይችላል።”
“የሩጫውን ሁኔታ እየነበባችሁ፤ የአሰልጣኞችን ምክር እየሰማችሁ”
አትሌት  ኢብራሂም ጀይለን
“በ10ሺና በ5ሺ ሜትር ምርጡ ሰዓት እኛ ጋር ነው.. ሩጫ ስነልቦና ነው አንታማም። ሁሉም የሚፈራው እኛን ነው።
አትሌት ሙክታር ኢድሪስ
“በርቱ እንደምታሸንፉ ተስፋ አደርጋለሁ። አረንጓዴ ጎርፍ እጠብቃለሁ”
አትሌት ማሬ ዲባባ
“አንድነታችንን ህብረታችንን ዓለም ያውቀዋል።”
“ውጤቱ ከመጣ፤ ባንዲራው ይመጣል። እርስበርስ ከተፈቃቀርን ውጤት እናመጣለን። ለዚህም የማራቶን ቡድናችን አርአያ ነው።”
“ለአገር መሮጥ በጣም ልዮ ነው።”
ገዛሐኝ አበራ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት (የቴክኒክ ቡድን መሪ)
“ዓለም ሻምፒዮናው ታክቲካል ነው። በመደጋገፍ ነው የሮጥነው፤ ስነልቦናና ትብብሩ ትልቅ ድርሻ ይወስዳል።”
አትሌት  የማነ ፀጋዬ
ለኢትዮጵያ የቡዳፔስት ልዑካን የሰንደቅ ዓላማ ርክክብ ላይ
“አትሌቲክስ የኢትዮጵያ ክብር፤ የኢትዮጵያ ሞገስ ነው። ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ የምንሄድበት ነው።”
“በጋራ ለምትሮጡት እኩል ነው የምንሸልመው።”
የኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ
“የአትሌቲክስ የኢትዮጵያ ስፖርት የጀርባ አጥንት ነው። በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ... የኢትዮጵያን ገፅታ በማስተዋወቅ በዲፕሎማሲ በመሥራት አስተዋጽኦ አድርጓል”
“ዘንድሮ ተጨማሪ ሜዳልያ ነው የምንጠብቀው፤ እድገት ማሳየት አለብን።”
“የትራክ ችግርን ለመቅረፍ የአዲስ አበባ ስታድዬምን እየገነባን ነው። የሚቀጥለውን ኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒዮን ልምምድ በዚያ ነው የምትሠሩት።”
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ቀጀላ መርጋሳ

Read 422 times