Friday, 25 August 2023 15:00

በደሌ ስፔሻል አዲሱን የገፅታ ዲዛይን አስተዋወቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)
በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የፕሪሚየም ቢራ ብራንድ የሆነው በደሌ ስፔሻል፤ አዲሱን የገፅታ ዲዛይን ትላንት ይፋ አደረገ፡፡ በአዲሱ የገፅታ ዲዛይን በደሌ ስፔሻል፣ ድምቀትና ዘመናዊ ቀለሞችን ተላብሶ ነው የቀረበው ተብሏል።
በደሌ ስፔሻል፣ ሃይንክን ኢትዮጵያ፣ ወደ ውጭ በሚላክ ስታንዳርድ (Export Standard) የሚያመርተው የሀገር ውስጥ ፕሪሚየም ብራንድ ሲሆን፤ የአልኮል ይዘቱ 5.5 በመቶ ነው።
የበደሌ ስፔሻል የልዩ ጣዕም መገለጫው ምስጢር፣ ከሁለት የተለያዩ የጌሾ ዝርያዎችና መቶ በመቶ ክተፈጥሯዊ ግብአቶች መጠመቁ ነው ተብሏል።
የሃይንከን ኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ፈለቀ፤ የበደሌ ስፔሻል አዲሱን የገፅታ ዲዛይን በማስተዋወቃችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል። አክለውም፤ “አዲሱ ዲዛይን የበደሌ ስፔሻልን አዲስነት፣ ጥራትና ዘመናዊ መንፈስ ያንፀባርቃል። በደሌ ስፔሻል ደፋር፣ ዘናጭና ዘመናዊ ቢራ ነው።” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
“ይህ የቢራዉ ዲዛይን (ሌብል) ማሻሻያ የደንበኞቻችንን ፍላጎት እያሟላን ለመቀጠል፣ እንዲሁም ለፈጠራና ለጥራት ያለንን ቁርጠኝነትና ፍላጎት ይሳያል” ብለዋል፤አቶ ካሳሁን፡፡
አዲሱ የበደሌ ስፔሻል የገፅታ ዲዛይን ሃሙስ ነሃሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በይፋ ተመርቋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 1941 times