Friday, 06 October 2023 00:00

አይቴል ሞባይል ኢትዮጵያ ለሙዳይ በጎ አድራጎት የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፎች አደረገ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከሚያቀርቡ ታላላቅ የሞባይል አምራች ኩባንያዎች አንዱ የሆነው አይቴል ሞባይል፤ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን የተለያዩ የትምህርትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ  ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር አስረክቧል፡፡
 አይቴል ሞባይል “ሁሌም ፍቅር” (Love Always) የሚል መርህ በማንገብ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚቀጥለውን ትውልድ በትምህርት ለማነፅ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ የማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ መርሃ ግብሮችን ያከናውናል። ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር የተደረገው ድጋፍም ኩባንያው የማህበራዊ ሀላፊነት ድርሻውን ለመወጣት ከሚሰራቸው ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች አንዱ የሆነው የሴቶችና ህጻናት ማዕከላትን ድጋፍ የመስጠት ስራ አካል ነው፡፡
 አይቴል ሞባይል ያስረከባቸው ቁሳቁሶች ከ500 በላይ ህጻናት፣ ታዳጊ ተማሪዎች እንዲሁም ሴቶችን ተጠቃሚ በማድረግ፣ ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር የሚሰራቸውን ስራዎች ለማገዝ የበኩሉን አስተዋፅዖ የሚያደርግ ይሆናል ተብሏል።
በርክክቡ ወቅት የአይቴል ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር ሚስተር ኤመን ጃ እንዳሉት፤ ህጻናቶችንና እናቶችን መደገፍ ለቤተሰብ ደህንነት ትልቅ ትርጉም ያለው በመሆኑ አይቴል ሞባይል ኩባንያ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
የማህበሩ መስራችና ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ በበኩላቸው፤ አይቴል ሞባይል ኢትዮጵያ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልፀው፣ ኩባንያው የሚያደርገው ድጋፍ ቀጣይነት እንዲኖረውም ጥሪ አቅርበዋል።  
በ1992 ዓ.ም. ኮተቤ አካባቢ በአጸደ ሕፃናት ትምህርት ቤት፣ ጥቂት ሕፃናትን በማስተማር የበጎ አድራጎት ሥራን አንድ ብሎ የጀመረው ሙዳይ የበጎ አድራጎት ማኅበር፣ ላለፉት 23 ዓመታት እናቶችንና  ሕጻናትን ማዕከል ባደረገ መልኩ ተጨባጭ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

Read 1191 times