• በሃማስ ጥቃት የተገደሉ እስራኤላውያን ቁጥር 1300 የደረሰ ሲሆን፤ ከ3ሺ 300 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡
• በእስራኤል የአየር ድብደባ የሞቱ ፍልስጤማውያን ቁጥር 1ሺ 500 የደረሰ ሲሆን፤ 5ሺ 600 ሰዎች ቆስለዋል፡፡
• በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት 27 አሜሪካውያን ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በሃማስ ከታገቱት ከ150 በላይ ሰዎች ውስጥ አሜሪካውያን ይገኙበታል፡፡
• የእስራኤል የጦር ም/ቤት ሃማስን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ክፉኛ ዝቷል፡፡
• “በአጭርና ግልፅ ቋንቋ አሜሪካ የእስራኤል አጋር ናት” - የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር
• ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ወደ እስራኤል የላከችው አሜሪካ፤ አውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከቧንም ወደ እስራኤል አስጠግታለች፡፡
• “አሜሪካ በፍልስጤም ህዝብ ላይ በሚደረገው ወረራ እየተሳተፈች ነው” - ሃማስ
• በጋዛ የምግብ፣ ውሃ፣ መድሃኒትና ነዳጅ አቅርቦት ተቋርጧል፡፡
• በእስራኤል የአየር ድበደባ 4238ሺ ፍልስጤማውያን ከጋዛ ተፈናቅለዋል - የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ
• እስራኤል በምድር ውጊያ ለማካሄድ 300ሺ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ ድንበር አስጠግታለች፡፡
• ሃማስ ጥቃቱን ለመመከት ዝግጁ ነኝ ብሏል፡፡
• “የሃማስ ብቸኛው አጀንዳ እስራኤልን ማጥፋትና አይሁዶችን መግደል ነው” -አንቶኒ ብሊንከን
• “እያንዳንዱ የሃማስ አባል በሞት ጥላ ሥር ነው” - የእስራኤል ጠ/ ሚኒስትር
• ሃማስ ጥቃት ከመፈጸሙ ከቀናት በፊት ግብፅ እስራኤልን አስጠንቅቃ ነበር - አሜሪካ
• እስራኤል 1.1 ሚ. ፍልስጤማውያን በ24 ሰዓት ውስጥ ከጋዛ እንዲወጡ አስጠነቀቀች፡፡
• የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት፣ በእስራኤልና ሃማስ ግጭት ላይ ለመምከር ዛሬ የዝግ ስብሰባ ያደርጋል፡፡
Published in
ዜና