Friday, 20 October 2023 07:56

ካቻ የተሰኘ የዲጂታል ፋይናንሲንግ ሰርቪስ አገልግሎቱን በይፋ አስጀመረ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ካቻ የተሰኘ የዲጂታል ፋይናንሲንግ ሰርቪስ የግል ክፍያ ሰነድ አውጪ በመሆን አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል። በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለው አገልግሎቱ ከብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፈቃድ ያገኘ እና የሞባይል የገንዘብ ዝውውርና ሌሎች የፋይናንስ አገልግሎቶችን በተለያየ ደረጃና አማራጮች ያካተተ መሆኑ ታውቋል።

ይህን ተከትሎ በካቻና በተለያዩ ባንኮች፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እና ሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር በጋራ አብሮ ለመስራት የፊርማ ሥነ ስርዓት ተካሂዷል።

በተጨማሪም ካቻ ከአለም አቀፍ ሓዋላ አስተላላፊዎች ጋር የፈጠረውን አጋርነት ያሳየው ደህንነቱ የተጠበቀ የውጪ ሓዋላን በማሳለጥ፤ ላኪዎችም ሆኑ ተቀባዮች ለተጨማሪ የፋይናንስ አገልግሎቶች ዕድል የሚያገኙበት አሰራር መዘርጋቱን ገልጿል።

የካቻ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተሾመ በየነ የካቻ ዓላማ ለደንበኞች በላቀ ቴክኖሎጂ የታገዘ ደህንነቱ የተጠበቀና የፋይናንስ አካታችነት ያለው የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ማቅረብ ነው ብለዋል

Read 1270 times