Friday, 20 October 2023 14:53

ለአእምሮ ጤና እንሮጣለን

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ሁልጊዜ በየዓመቱ እ.ኤ.አ ጥቅምት 10 ቀን የሚከበረው የአእምሮ ጤና ቀን ዓለማቀፋዊ ኢኒሸቲቭ ያለው ሆኖ በተለያዩ መሪ ቃሎችና ዝግጅቶች ይከበራል፡፡ የ2016 የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን የአእምሮ ጤና ዓለማቀፋዊ ሰብዓዊ መብት ነው በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል ፡፡

ይህንን ቀን የአማኑኤል አእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከጤና ሚ/ር፤ ከማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን እና ከሌሎችም አጋርና ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን በ4/2/2015 ዓ.ም  ካሳንችስ በሚገኘው ሰላም መንገድ ላይ የተለያዩ የመንግስት መ/ቤትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅት ሰራተኞች ያሳተፈ የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ የማስ ሩጫ ፌስቲቫል አካሂዷል፡፡

የፌስቲቫሉ ዋና ዓላማ ማንኛውም የማህበረሰብ አካል የአእምሮ ጤና ጉዳይ የእኔም ጉዳይ ነው ይመለከተኛል ብሎ በመውሰድ የአእምሮ ጤና አጠባበቅ መሰረታዊ ሰብዓዊ መብት መሆኑን በመረዳት በአእምሮ ህሙማን ላይ የሚደርሰውን አድሎና መገለል መከላከል እንደሚገባ ለማስገንዘብ ያለመ ነው፡፡ በመሆኑም የአእምሮ ህሙማን ማንኛውም ሰው ልጅ ያለውና ሊከበርለት የሚገቡት ሰብዓዊ መብቶች እንዲሁ ሊከበሩላቸው እንደሚገባም በፌስቲቫሉ ተንፀባርቋል፡፡

ለአእምሮ ጤና መጠበቅና መጎልበት  እንዲሁም ለአእምሮ ህሙማን ሰብዓዊ መብት መከበርና መረጋገጥ ሁልጊዜም ግንባር ቀደም በመሆን ልንሮጥ ይገባል!!!

Samuel Tolossa
የአማኑኤል ሆስፒታል ተመላላሽ ህክምና ዳሬክተር

Read 650 times