Tuesday, 12 December 2023 20:11

የአክሱምን ሥልጣኔን ለመመሥከርየመካከለኛውን ዘመን ከፍታ መካድ ምንድነው ጥቅሙ?

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ዚያ ልክ በምስራቃውያን የተመስጦ ብርሃን የሚመላለስ መናኒ፥በዚህ ልክ አድሎአዊ እንዴት ሊሆን ይችላል? ሊገባኝ አልቻለም! ያዕቆብ ብርሃኑ “የፍምእሳት ማቃመስ” በሚለው 5ኛው መጽሐፉ የታሪክ ክፍሉ ላይ ያነሳቸው የታሪክ ሰበዞችሚዛናቸውን የሳቱና የግል አሉታዊሥሜት የተንጸባረቀባቸው፣ በመሰለኝና በደሳለኝ መንፈስየተጻፉ መሆናቸው የመጽሐፉን መንፈስ ይረብሸዋል። የመጽሐፉ የሕትመት ወረቀት ጥራትና
የሥነ ጽሑፍ ውበቱ እጅግ ግሩም ነው። በምሥራቃውያን ብህትውናዊ የሕይወት ፍልስፍና ላይ ያለው ንባብና ተመስጦ በእጅጉ ያስቀናል። ዳሩ ግን የመጽሐፉ የእርስ በእርስ የሃሳብ ግጭትና ያለ በቂ መረጃ የሚደመድመው ነገር የመጽሐፉን ትልቅነት የሚቀንሰው ይመስለኛል። አንዳንድ ጊዜ ግልጽ ተቃርኖዎችን በንጹህ ሕሊናህ ለማስታረቅ ወይም ለማቀራረብ ዳኛ ስታጣ ስለ ፍትህ ብለህ የራስህን ብይን ትሰጣለህ። በእኔ ትንሿ የታሪክ ንባቤ፥ ያዕቆብ ብርሃኑ የታሪክ ትንተናውን ቢተወው የመጽሐፉን ዋጋ ያንረዋል ብዬ አስባለሁ። ስለ አንድ ሁነት ከታሪክ ተነስቶ ብይን ለመስጠት ታሪክን
በከፍተኛ ጥንቃቄ በወጉ የግድ ማወቅ ይኖርበታል። ታሪክ በነጠላ ጥራዝ ነጠቅ ጥቅስ ድምዳሜ ላይ አይደርስም። “ማኒ” አክሱም ኃያል ነች ስላለ ብቻ ኃያል ነች ብለን ስናወድስ፣ “ኤዲዋርዶ ጊበን” ደግሞ የመካከለኛው ዘመን ጨለማ ነው ስላለ ብቻ ጨለማ ነው ብለን ስንረግም መኖርየለብንም። እንደ ሀገርና እንደ ማኅበረሰብም የጎዳን ይህ አይነቱ የጠቅላይ ድምዳሜ አካሄድ ነው። ይህ ስለ አክሱምና መካከለኛው ዘመንበዶ/ር ዳኛቸው አሰፋና በብሩህ አለምነህ የተደረገው ስሁት የታሪክ ድምዳሜ እንደገና ከታሪክ መነሻው መታየት ያለበት ጉዳይ ሆኖሳለ እንደገና ያዕቆብ ብርሃኑ ደግሞ ጥናት
ሳያደርግ ሲደግመውታሪክ ከባለሙያ ውጭ ሲታይ የሚያመጣውን የተዛነፈ ድምዳሜን ያረጋግጥልናል። አክሱምን በጥልቀት ሳያውቁ ስለአክሱም ድምዳሜ መስጠት፣ መካከለኛውዘመንን በጥልቀት ሳያጠኑ ስለ መካከለኛው ዘመን ስሁት ድምዳሜ መስጠት እንዴት ይቻላል? ይህ አይነቱ አካሄያድ ምንድነው ጥቅሙ? ማንንስ ነው የሚጠቅመው? ለምሳሌ ያዕቆብ እንዲህ ይላል፤...”ለነገሩ እስከ አፄ ቴዎድሮስ ዘመን ያለውየኢትዮጵያ ታሪክ በሙሉ ትረካው ተረትቅልቅል ነው” (ገጽ 7) ይላል። የትኛውታሪክ ነው ተረቱ? በንጽጽር የመካከለኛውዘመን ከየትኛውም ጊዜ በላይ ለኢትዮጵያየታሪክ ጥናት በቂ የጽሑፍና የቁሳቁስ ምንጮች ያሉበት በመሆኑ ከተረት የጸዳ ታሪክ መጻፍ የሚቻልበት አቅም አለው። በዚህም የተነሳ እነ ፕሮፌሰር ሥርግው
ኃብለ ሥላሴ፣ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት፣ ፕሮፌሰር መርዕድ ወልዳረጋይ፣ ተክለጻዲቅ መኩሪያ፣ ዳንኤል ክብረት፣ ፕሮፌሰርሀብታሙ መንግሥቴ፤ ከውጭ የታሪክ ጸሐፊያን ደግሞ ኤድዋርድ ኡሉንዶርፍ፣ ትሪሚንግሃም፣ ኮንቲ ሮሲኒና ሌሎችም የዘመናዊ የታሪክ ጥናት መንገድን በመከተልከተረት በላይ የሆነ ታሪክ በማስረጃ ጽፈዋል! ነገር ግን ለታሪክ ምንጭነት እንደ ግብዓት የሚያገለግሉ ዜና መዋዕልን፣ ገድላትን፣የተለያዩ ድርሳናትን፣ ሚት ነክ
እና የዘውጌ ትርክቶችን እንደ መደበኛ ታሪክ ማየት እጅግ አደገኛ ነው። እነዚህ ከላይ የዘረዘርናቸው ድርሳናት በየትኛውምሀገር ያሉ ሁነቶች ናቸው።ይልቁንም በበቂመረጃ ያልደገፈውና መካከለኛው ዘመንንያነቃቃው፣ ያዕቆብ ስለ ንግሥተ ሳባናስለ አክሱም የጻፈው ተረክ ነው። በጣም
የሚገርመው ለሚፈልገው ዓላማ ሲሆን ተረት የተባለውን እንደ እውነት መጠቀም ደስ ያላለውን ዘመን ደግሞ በመደበኛ የታሪክ ባለሙያዎች የተጻፈውን ኃቃዊ ታሪክ እንደ ተረት መቁጠር ምን የሚባል ሳይንስ ነው?
“በአባቷ እግር የተተካችው ንግሥተ ሳባ ግን ቅድመ አክሱም ኢትዮጵያን ታላቅ አደረገች” ይላል (ገጽ 8) ላይ። ንግሥተ ሳባ መቼ እና የት ቦታ እንዴት ባለ ንግሥና ነገሰች? የሚለው ተረክ ግን በበቂ ማስረጃ ማሳየት አይቻልም። ያዕቆብም አንዲትምየእናት መዝገም ማስረጃ አላቀረበም።
ቅድመ አክሱም ንግሥተ ሳባኢትዮጵያንኃያል አደረገች የሚለው ተረክ በእምነትና በሚትእንጅ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ “በአባቷ እግር የተተካችው ንግሥተ ሳባ ግን ቅድመ አክሱም ኢትዮጵያን ታላቅ አደረገች” ይላል (ገጽ 8) ላይ። ንግሥተ ሳባ መቼ እና የት ቦታ እንዴት ባለ ንግሥናነገሰች? የሚለው ተረክ ግን በበቂ ማስረጃ ማሳየት አይቻልም። ያዕቆብም አንዲትም የእናት መዝገም ማስረጃ አላቀረበም። ቅድመ አክሱም ንግሥተ ሳባኢትዮጵያን ኃያል አደረገች የሚለው ተረክ በእምነትና በሚትእንጅ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም። ዳሩ ግን መረጃ የለም ብለንተረኩ ውሸት ነው የሚል ድምዳሜ ላይ አንደርስም። ይቀጥልና ከአክሱም መውደቅ በኋላ፤ “ከዚያ በፊት ያልነበሩት የእርስ በርስ ጦርነቶች እንደ አሸን ፈሉ” (ገጽ11) ይለናል። ለዚህ ሃሳብ መነሻው ምንድ ነው? በጥንት ጊዜ የርስበርስ ጦርነት ያልነበረበት ጊዜ አለ ወይ? በአክሱማውያንዘመን ስለተደረጉት ጦርነቶች ምን ያህል ያውቃል? የኢዛና የድንጋይ ላይ ጽሑፎች እንኳን የተጻፈበት ከበርካታ ጎሳዎች ጋር ስላደረገው ጦርነት ድል ነው። በአክሱም
ዘመን የኢትዮጵያ ጂኦግራፊካል ግዛት ምን ያህል ነበር? ሚጢጢዬ? ወይም ሰፊ?እንደሆነ እንኳን በእርግጠኝነት መናገር የሚችል አካልየለም።መረጃ ካለ በበቂ መረጃ መሞገት ይችላል። መካከለኛው ዘመን ግን በተለይም የዓምደ ጽዮንና የዘርዓ ያዕቆብ ዘመን በጣም ትንሽ የነበረችውንየአክሱም ኢትዮጵያግዛት ለማስፋፋት ትላልቅ ዘመቻዎችን አከናውነዋል ይሁንና ይኸ ዘመቻ የኢትዮጵያን የሃገረ መንግሥት ግንባታ ከፍታን ያሳያል እንጅ የውድቀት አንድምታ የለውም። ፕሮፌሰር ኡሉንዶርፍና ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛ እምርታ የታየበት ዘመን እንደነበር ጽፈዋል። በተለይም ዳንኤል ክብረት “ከእቴጌ ዕሌኒ እስከ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ” በሚለው መጽሐፉና ፕሮፌሰር ሀብታሙ መንግሥቴ”በረራ-ቀዳሚት አዲስ
አበባ”በሚለው መጽሐፍ የመካከለኛውን ዘመንን ከፍታ በእናት መዝገብ በመታገዝ በዝርዝር አስቀምጠዋል! እስካሁን ይኸንን ያስተባበለ ምሁር አልመጣም።
ያዕቆብ ይቀጥልና፤ “የአክሱም ሥልጣኔ ግን አንድ ሥልጣኔ ሊኖረው የሚገባው ቅንጣቶች ሁሉ ነበሩት ...የተደራጀ ሥነ መንግሥት፣ የጽሕፈት ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ዕደ ጥበብ፣ የንግድ ግንኙነት፣ፈጠራ፣ ከተሞች ...” ሲኖሩት የመካከለኛው ዘመን እንደሌለው ይናገራል። የአክሱም መንግሥት የነበሩት የእድገት ምልክቶች የዛጉዌም፣ የሸዋም ሆነ የጎንደር የአፄ ግዛት ነበሯቸው። እነዚህ የአክሱም ቀጥታዊ ወራሽ በመሆናቸው የአክሱም የሥልጣኔ አብዛኛው ቅንጣቶች ነበራቸው። እዚህ ድምዳሜ ላይ ከመድረሳችን በፊት በመካከለኛው ዘመን የነበረውን የሀገረ መንግሥት ግንባታ፣የዕውቀት ግስጋሴ፣ የዲፕሎማሲ ጉዞ፣ የከተማ ግንባታዎች፣የሥነ -ጽሁፍ፣ የውይይት እድገት እና መሰል ታሪኮችን ቁጭ ብለን ከበዛው መረጃ ማጥናት
ይጠበቅብናል። ደግሞም የገብረሕይወት ባይከዳኝን፣ የዳንኤል ክብረትን፣የኤድዋርዶ ኡለንዶርፍን፣ የሀብታሙ መንግሥቴን ጥናት እና እጅግ ብዙ ያልተጠኑ የጽሁፍ ስራዎችን ማፈራረስ ያስፈልጋል። አለበለዚያ እንደዚህ የማለት ሞራል ሊኖር አይችልም።
ያዕቆብ፥ የደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን እንቅስቃሴ የፕሮቴስታንታዊ የለውጥ አቀንቃኝ አድርጎ ማቅረብ ይታይበታል! (ገጽ 22)። ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን እኮ ዋናው አጀንዳቸው ይህን ዓለም ንቆና ጥሎ በባሕታዊነት መመነን መሆኑን ማየት ለምን እንዳልተቻለ ትልቅ ጥያቄ ነው? ስለ ደቂቀ
እስጢፋኖሳውያን ዋና አጀንዳ በአማን ነጸረ በ”ወልታ ጽድቅ” መጽሐፉ በእናት መዝገብ አማካኝነት ይኸን የውሸት መረጃ አልባ ትርክት አፈራርሶታል!
ያዕቆብ ይቀጥልና”በዚያ በኢሮፓ ሼክስፒር...በጻፈበት ዘመን በኢትዮጵያ ደብተሮች የአጼ ልብነ ድንግልንና የአጼ ገላውዲዎስን ዜና መዋዕል እና ገድሎች
መልካመልኮች ይደርቱ ነበር” ገጽ 28 እና ገጽ 47 ይላል። ዜና መዋዕል፣ገድልና መልክ በዚያ ዘመን መጻፍ እኮ ያስደንቃል እንጅ“ይደርቱ” ነበር ተብሎ አያሰድብም ነበር። ትልቁ ችግር በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እነዚህን የጽሁፍ ሥራዎችን እንኳን በወጉ የሚያጠና ኢትዮጵያዊ ሰው አለመኖሩ ነው። እነዚህን ሥራዎች እንኳን በማድነቅ የተራቀቁባቸው ፈረንጆቹ የመሆናቸውን ጉዳይ ስናጠና አንድ ኢትዮጵያዊ ተነስቶስለማያውቀው ድርሳናት የመናገር ሞራል ማግኘቱ ኢ-ፍትሃዊ ነው። በጣም የሚገርመው ደግሞ ይኸ አገላለጽ ነው።”ሀገር የሚሰራው በትርክትነው ይልና...እኛ ግን በጠጅ ከሚወራረድየአባቶቻችን ገድል ከታከከ ፉከራ በቀርበአትሮኖሳችን ምንም ትርክት አልነበረም”(ገጽ 57 እና ገጽ 62) ይላል። በዚያን ዘመን
በዓለም ላይ ኢትዮጵያውያን አባቶች እኛታላቅ ሕዝብ ነን ብለው ክብረ ነገሥትንያህል መጽሐፍ ከመጻፍ የበለጠ ትርክት ምንሊያመጡ ይችላሉ? ኢትዮጵያውያን በጊዜውአሁን ኃያላን የሆኑት ሀገራት ከፈጠሩትትርክት የሚበልጥ ትርክት ፈጥረው ነበር።ዳሩ ግን ያንን ታላቅ ትርክ(Grandnarration ) የሁሉ በማድረግ ማስቀጠልናማሻሻል ባለመቻሉ ትርክት አልባ ሀገርናትውልድ ፈጥረናል። ይህ የአባቶች ችግር
ሳይሆን የኛ ችግር ነው። ኢትዮጵያውያንበፈጠሩት ጠንካራ የበላይነትን የሚያላብስትርክት የተነሳ ታላላቅ መንፈሳዊ ነገሥታትተፈጥረውም ነበር። በዚህም የተነሳ በአውሮፓውያን እንኳን ሳይቀር ‘የካህኑ ዮሐንስ’ ሀገር የሚል ገነታዊ ተምኔት የተላበሰ ግሩም ትርክት ፈጥረውልን ነበር፤ ይኸንንም
መጠቀም አልቻልንም። እንደውም ቀደምት ኢትዮጵያውያን የሚታሙት ለራሳቸው የተጋነነ ትርክት በመፍጠራቸው ነው እንጅ
ትርክት ባለመፍጠራቸው አይደለም።አንዳንድ ጊዜ ስለ ሰው ልጅ ንጽህና፣ ቅድስናና ተፈጥሮአዊነት በሚያስደንቅተመስጦ፡ሲጽፍምሳሌዎቹንባህር ተሻግሮ እነ ቅዱስ”ፍራንሲስኮ አሴሲ”እና”ቅድስት ቴሬዛን” ሲጠቅስ ጸሐፊው “ያዕቆብ ብርሃኑ” በምን ያህል ደረጃ ከኢትዮጵያውያን የመናኒያን ድርሳናት
እንደራቀ ይጠቁመናል። ምናልባት የኢትዮጵያ ቅዱሳንን ተመስጦና ከተፈጥሮ ጋር ያላቸውን ኅብረት አይቶት ቢሆን ኖሮ ምሳሌ ለመጥቀስ ባሕር አይሻገርም ነበር። ኢትዮጵያ አንዱ የምትተችበት እኮ ቁሳዊ ሥልጣኔን ትታ በርካታ መናኒያንና ጻደቃንን ያፈራች መንፈሳዊት ሀገር መሆኗ ነው። ከኢትዮጵያ ርቆ ስለ ኢትዮጵያ መጻፍ አንዱና ዋናው ችግራችን ነው።
ደራሲው ያዕቆብ ብርሃኑ በአንድ በኩል የኢትዮጵያ በቁስ አለመሰልጠኗ እጅግ እያሳስበው ትችት ያቀርባል፤ በሌላ መለኩ ደግሞ የምዕራባውያንን ሥልጣኔ “ስይጠና”(ሠይጣንነት) ይለዋል፤ አክሎም የሰው ልጅ ወደ ተፈጥሮአዊነት መመለስ አለበት ብሎ ይከራከራል።”የሰው ልጅ ወደ ዋሻው፣ ወደ
ምንጩ፣ ወደ ሥነ ተፈጥሮው ወደ ንጽሕና ልጅነት መመለስ እንዳለበት አስባለሁ” ይላል ገጽ 84። ይህ የመጽሐፉን ጭብጥ እርስበርሱእንዲጋጭ ያደርገዋል! በአንድ ወገን አውሮፓውያን ሲሰለጥኑ ኢትዮጵያ ምንኩስና ላይ ነበረች በማለት ይተቻል፣ በሌላ መንገድ ደግሞ በጥልቅ መመሰጥንና
ከተፈጥሮ ጋር ኅብረት መፍጠርን እሴቱ ያደረገውን ምንኩስናን በጥልቅ መቃተት ይናፍቀዋል፤ እንደገና ደግሞ የአውሮፓ ሥልጣኔ “ሥይጠና” ነው በማለት ያጣጥለዋል። ታዲያ እርስበርሱ የሚቃረን ሃሳብ ካቀረበ የጸሐፊው ጭብጥ ምንድነው? ይልቅ በዚህ በኩል ሺህ ጊዜ ቢጽፍ ሺህና ሺህ ጊዜ የሚያነቡት ደቀመዛሙርት ሲያፈራ እንደሚኖር አልጠራጠርም። ያዕቆብ ብርሃኑ እንዲህ ይለናል፡- “የሆነ ሰው ... ይሄን ሁሉ ዘመን ምን ስታደርግ ነበር ? ቢለኝ በእብዶች ጉባኤ በታወከች ከተማ፣ ሀገር፣ ዓለም መሃል ነፍሴን የማስጠልልባት የሆነች የጽሞና ጥጋት ሳስስ ነበር” ገጽ 108። ይቀጥልና”ሌላ ሰው ደግሞ አንተ ማነህ ቢለኝ መልሴ “የጽሞና አሳሽ ነኝ” ማለት ይከጅለኛል” ገጽ 111።“ ቢሆንም የጽሞናው አሳሽ ነኝ፣እስኪይዘኝ መሄድ እፈልጋለሁ፣ ነፍሴን የማስጠልልባት የፀጥታ ጥጋት እስካገኝ ወደ ምንም መራመድ ያምረኛል” ገጽ 113። ይህ የጽሞና አሳሽ ከሰውና ከኳኳታው እየሸሸ፣ በአካይ ሌሊት ከተማዋን በጽሞና የሚታዘብ! ከጸጥታው ጋር ቅጽበቶችን የሚዋረስ! ታዲያ ይኸ ሰው በታሪክ ላይ የሚያዳላ አንጀትን ከየት አመጣው? ከተፈጥሮ ውብ ምስጢራት ጋር እና ከዚያ ባሻገር ካለው ኃይል ጋር ኅብረት ለመፍጠርና ለመነጋገር የሚያደርገውን
መፍገምገም በድንቅ ቃል እንዲህ ሲናገረው ያምራል! እግዚአብሔርን ስትሹ፥”ከእያንዳንዷ ቢራቢሮ ጋር ለመቅበጥበጥ፣ ከእያንዳንዷ አበባ ጋር ለመሽኮርመም.... እናም ወደ ተራሮች የመሸሽ ምኞት እንዳልሆነ እወቁት...በፍጹም እዚያ ተፈጥሮ ነው፤ እዚያ ንጹህ ትንፋሽ፤ ወደ ተራሮች መውጣት
የሚያርበተብት መሻት ነው፣ ወደ ተፈጥሮ የመመለስ ፍንደቃ፣ በኦና የብርሃን ንኝት የመስከር፣ ፀሐይ እንዳኮረፈች ልጃገረድ ከተራሮች ጀርባ ስትጋረድ፣ ጨለማ ከሸለቆዎች ጥልቅ እየዳኸ ወጥቶ መላውን ፍጥረት ሲቆጣጠር የመመልከት መቋመጥ...ራሮች ወንድሞቻችን ናቸው። አዎ ከደመና
ለመተቃቀፍ፣ ከጉም ለመሳሳም፣ ጨረቃን ለማሽኮርመም፣ ፀሐይን ለማሞር፣ በእግዜር ችሎት ላይ ለመታደም ከፍታውን እፈልገዋለሁ” ይላል። (ገጽ 146)። ይኸኛው አይነት ሮማንቲክ አጻጻፍ መቼም ቢሆን ወረቱ የማይቀዘቅዝ ኪነ ጥበባዊ አጻጻፍ ስለሆነ ይበል የሚያሰኝ ነው። የተፈጥሮን ህልቆ መሳፍርት ምስጢር እያሰሱ መኖር አለፍም ሲል ሕብረታዊ መቃመስን በመፍጠር ሁኔታው በብዕር እንዲህ መሰደር ይታደሉታል እንጅ አይሸከሙትም። ያዕቆብ ብርሃኑ በዚህ በኩል በጻፈ ጊዜ ቀልብን ሰቅዞ ይይዛል! ያዕቆብ ብርሃኑ በዚህ መጽሐፍ ተተኳሪነት በ”ዐውደ ፋጎስ የውይይትክበብ” ላይ”ኢትዮጵያውያን ከእሳት ዳርሥልጣኔ ምን አተረፍን? ምን አዋጣን? ምንስ አጎደለብን?” በሚል ርዕስ ቁጭትንየሚፈጥር ምርጥ የውይይት መነሻ ገለጻ አድርጎ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ነበር። ምን አልባትም የታሪክ ክፍሉ ውይይት ላይ ቀርቦ ቢሆን ኑሮ ትላልቅ ግልጽ ግብአት ይገኝበትነበር። ሌላው በመጽሐፉ የመጨረሻምዕራፍ “በፍም እሳት ማቃመስ” በሚለውርእስ ስር የቀረበው የአልኬሚ ትንታኔመሰረቱን ምን አድርጎ እንደሚተነትን ግልጽ
አይደለም። ሃሳቡ የፈጠራ ይሁን የመገለጥወይም የግል አስተውሎት ምንም ግልጽ አይደለም። ለኃቃዊ ምልከታ ትችት በሰፊውየተጋለጠ ጽሁፍ እንደሆነ ይሰማኛል። እንደ ማጠቃለያ:- ያዕቆብ ብርሃኑ በታሪክ ዙሪያ ያነሳው ሃተታና ብያኔ ሚዛናዊነት የጎደለውና የግል ስሜት የተጫነው በመሆኑ በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተመሰጠባቸው ረቂቃን የሚስቲሲዝም ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ጥላ ያጠላባቸዋል! በዚያ ልክበጥልቀት የሚመሰጥና ከተፈጥሮ
ውበት ጋር ሊቃመስ የሚፍጨረጨር ባህታዊ አከል ደራሲ እንዴት ኢ-ፍትሃዊ ፖለቲካ ቀመስ የሚመስል የፕሮፓጋንዳ የታሪክ ብይን ሊጽፍ ይችላል?

Read 431 times