Wednesday, 13 December 2023 16:41

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከ2 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ መጋለጡን አስታወቀ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

•  በትግራይ የተከሰተው ድርቅ ከ77ቱ የከፋ ነው ተባለ  

•  25 ህፃናትን ጨምሮ 400 ሰዎች በረሃብ   ሞተዋል  

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በክልሉ   ከ2 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ መጋለጡን ያስታወቀ ሲሆን፤ እስካሁንም 23 ህጻናትን ጨምሮ 400 ሰዎች በረሃብ መሞታቸውን ጠቁሟል፡፡

በክልሉ ያጋጠመውን የድርቅ አደጋ ለመከላከል ያለመ፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ  22 አባላት ያሉት "አፋጣኝ ምላሽ ለትግራይ" የተሰኘ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እንቅስቃሴ መጀመሩም ተነግሯል፡፡

የ"አፈጣኝ ምላሽ ለትግራይ" ግብረ ሃይል ሰብሳቢ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ   በዛሬው ዕለት  ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ በአሁኑ ሰአት ለረሃብ አደጋ የተጋለጠውን ከ2 ሚሊዮን በላይ ትግራዋይ ህይወት ለመታደግ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኝ የክልሉ ተወላጅና ወዳጅ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።  “ሰብዓዊነት የሚሰማው ሁሉ” የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋም ጠይቀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር ገብረሕይወት ገ/እግዚአብሔር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ድርቁ በአምስት የትግራይ ክልል ዞኖች ተከስቷል ብለዋል።


“በትግራይ የከፋው ድርቅ የተከሰተው በ1951 እና በ1977 ነበር፤ አሁን ያጋጠመን ከዚያም በላይ ነው፤ በዚህ ድርቅ ምክንያት 2 ሚሊዮን ሕዝብ ተርቧል። 400 የሚሆኑ ሰዎች ባለፈው ወር ብቻ  በረሃብ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል” ብለዋል፤ ኮሚሽነሩ፡፡

የ"አፈጣኝ ምላሽ ለትግራይ" ግብረ ሃይል ድጋፍ ማሰባሰቢያ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች የሚከተሉር ናቸው፡-

* አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ፡-00112180095-49

* ወጋገን ባንክ፡- 1001077411101

* የኢትዮጵያ  ንግድ ባንክ፡- 1000592420809

Read 1470 times