Saturday, 16 December 2023 20:34

በ33ኛው ኦሎምፒያድ መክፈቻ ስነስርዓት ከ600ሺ በላይ ሕዝብ ለማሳተፍ ታቅዷል

Written by  ግሩም ሰይፉ
Rate this item
(0 votes)

ፓሪስ በምታደርገው ዝግጅት ከ5 ቢሊየን ዶላር በላይ ወጭ ሆኗል። ከ6.8 ሚሊዮን በላይ ትኬቶች ተሸጠዋል፤ ከአገር ውስጥ ስፖንሰሮችከ1.1 ቢሊየን ዶላር በላይ ተሰብስቧል። ፓሪስ ለምታስተናግደው 33 ኛው ኦሎምፒያድ 223 ቀናት ቀርተዋል። የፓሪስ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የመክፈቻ ስነስርዓቱን
በታሪክ ለማስመዝገብ መዘጋጀቱን አስታውቋል። በተያዘው እቅድ መሰረት የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ 10 ሺ ኦሎምፒያኖች በሴና አድርገው መሐል ፓሪስ ድረስ በጀልባዎች የሚጓዙ ይሆናል። በስታድየም የሚካሄደውን ዝግጅት ጨምሮ 600 ሺ ተመልካቾች መክፈቻውን በግንባር እንዲታደሙ ኘው የታቀደው። የፓሪስ ኦሎምፒክ አጠቃላይ ዝግጅት ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ በጀት ተደርጎለት እየተካሄደ ይገኛል። የፓሪስ ከተማ አስተዳደር ለኦሎምፒክ የተሳካ መሥተንግዶ ወጭ ያደረገው ከ43 ሚሊዮን ዶላር ማለፉም ይገለጻል። በኦሎምፒክ ከፍተኛው
የመስቸንግዶ ወጭ ሆኖ የተመዘገበው ቀ2016 ላይ ብራዚል ለ31ኛው ኦሎምፒያድ ወጭ ያደረገችው 11.1 ቢሊየን ዶላር ነው። ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ከ2024 ጀምሮ ለፓሪስ ኦሎምፒክ፤ ለ2026 የክረምት ኦሎምፒክና ለ2028 ሎሣንጀለስ ኦሎምፒክ ከተሞች ያማረ መስተንግዶ
ከ1.3 ቢሊየን ዶላር በላይ መድቧል። የፓሪስ ኦሎምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ እንዳስታወቀው ለኦሎምፒኩ ከ6.8 ሚሊዮን በላይ ትኬቶች መሸጣቸውንና ከአገር ውስጥ ስፖንሰሮች ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ መገኘቱን አስታውቋል። በ2021 ላይ ቶኪዮ ያስተናገደችው 31ኛው ኦሎምፒያድ ከ7.6
ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ሆኖበታል። ዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከታላቁ የስፖርት መድረክ ከሚያገኘው ገቢ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሆነውን ለአባል አገር ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ያከፋፍላል። የተለያዩ የኦሎምፒክ ስፖርቶች በዓለም ዙርያ ለማስፋፋት ተብሎ ደግሞበነፍስወከፍ ከ13 አስከ 17 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያበረክትም ታውቋል።


Read 192 times