Saturday, 13 January 2024 00:00

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ኮበለሉ የተባለው ሀሰተኛ መረጃ ነው ተባለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

“ብፁዕነታቸው የከተራና ጥምቀት በዓልን ለማክበር ወደ አሜሪካ አቅንተዋል”
                               
            ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዋና ፀኃፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ወደ አሜሪካ ማቅናታቸውን ተከትሎ፣ “አቡነ ጴጥሮስ ኮበለሉ” በሚል በማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ሲሰራጭ የሰነበተው መረጃ ሃሰተኛ መሆኑን ቤተክህነት አስታወቀች። የቤተ-ክርስቲያናት የህዝብ ግንኙነት መምሪያ በቅዱስነታቸው ላይ እየተሰራጨ ያለውን ሀሰተኛ መረጃ አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ “የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሐዋሪያዊ ጉዞ በቤተክርስቲያን ህግና ሥርዓት መሰረት የተፈቀደና እውቅና ያለው ነው፤ ቅዱስነታቸው በኒውዮርክና በአካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንደመሆናቸው የከተራንና ጥምቀትን በዓል ለማክበር ተጉዘዋል” ብሏል።  ይሁን እንጂ የቅዱስነታቸውን ጉዞ አስመልክቶ በማህራዊ ሚዲያ እየተናፈሰ ያለው መረጃ እጅግ የተሳሳተ መሆኑን የገለጸው የቤተ-ክርስቲያኗ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ፤ የብፁዕነታቸው ሀዋሪያዊ ጉዞ በቤተ-ክርስቲያን ህግና ሥርዓት መሰረት፣ በቅዱስ ፓትሪያርኩ የተፈቀደና በጠቅላይ ቤተክህነት የታወቀ መሆኑን አብራርቷል። መምሪያው አክሎም፤ ብፁዕነታቸው ሀዋሪያዊ ጉዟቸውን ሲያጠናቅቁ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱና የመደበኛ ፅህፈት ቤት ስራቸውን እንደሚመሩ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለፁን ጨምሮ ገልጿል።


Read 1158 times