Sunday, 28 January 2024 20:29

ቴክኖ ሞባይል “ስፓርክ 20 ፕሮፕላስ” ስማርት ሞባይልን አስተዋወቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የዘንድሮ የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ይፋዊ ስፖንሰር ነው

የሞባይል ቴክኖሎጂ ብራንዶች አምራቹ ቴክኖ ሞባይል፤ ሰሞኑን ስፓርክ 20 ፕሮ ፕላስ (Spark 20 Pro+) የተሰኘ አዲስ ስማርት ሞባይሉን ያስተዋወቀ ሲሆን፤ ምርቱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተራቀቀ፣ እጅግ ከፍተኛ የካሜራ ጥራትና የፕሮሰሰር አቅም እንዲሁም ለረጅም ጊዜ መቆየት የሚችል ባትሪ፣ ማራኪ ቅርጽና ውበት ያለው የመጨረሻው የቴክኖሎጂ ውጤት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ኩባንያው ደንበኞች የላቀ የአገልግሎት ተሞክሮ እንዲኖራቸው የሚያስችለውን አዲስ  የስማርት ሞባይል ስልክ ሞዴሉን  በአዲስ አበባ ፍሬንድሽፕ ፓርክ በደማቅ መርሃ ግብር  አስተዋውቋል።

ቴክኖ ሞባይል አዲሱን ስፓርክ ፕሮ ፕላስ ሞዴል ባስተዋወቀበት ልዩ ዝግጅት የመንግስት ባለስልጣናት፣ የቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ አንጋፋ የእግር ተጫዋቾችና አመራሮች እንዲሁም የስፖርቱ ቤተሰብ የታደሙ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የስፖርቱ ዘርፍ እድገትና የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ተሳትፎ እውን እንዲሆን ከፍተኛ ሚና የነበራቸውን የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞችና የስፖርት ጋዜጠኞችን የማመስገኛ መርሃ ግበር ያካተተም ነበር። በስፖርቱ አለም ተወዳጅ ከሚባሉት ዝግጅቶች አንዱ የሆነውን የአፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር ይፋዊ ስፖንሰር የሆነው ቴክኖ ሞባይል፤ ይህን አዲሱን የሞባይል ሞዴል ከዚሁ የአህጉራዊ ስፖርት መርሀ ግብር ጋር በማስተሳሰር ቴክኖሎጂና ስፖርቱን ያጣመረ የማስተዋወቅ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎችን በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እያከናወነ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አዲሱ ስፓርክ 20 ፕሮ ፕላስ ሞዴል፤ በ108 ሜጋ ፒክስል አልትራ ሴንሴቲቭ (ultra-sensitive) የካሜራ ጥራት የተገጠመለት ሲሆን፤ በኤ.አይ (AI) ሲስተም በመታገዝ በየትኛውም አይነት የብርሀን መጠን በምሽት ሆነ በቀን ጥርት ያሉ ፎቶዎችን ማንሳት የሚያስችል ሲሆን፤ በከፍተኛ ፍጥነት የተለያዩ መተግበሪያዎችን ያለ እንክን እንዲያስተናግድ የሚያስችለው (G99 ultra boost) የተሰኘ ፕሮሰሰር ያለው መሆኑና 6.78 ኢንች አሞሌድ ስክሪን በ120Hz ሪፍሬሽ ሬት የሆነው ስፓርክ 20 ፕሮ ፕላስ ሲጠቀሙበት ያለምንም እንከን በቅልጥፍና አንዲያገለግል ያደርገዋል ተብሏል። የሞዴሉንም የመያዝ አቅሙን በመጨመር 256 ጂቢ ሚሞሪ በ16 ጂቢ ራም ጋር የቀረበ ሲሆን፤ 5000 mAh አቅም ያለው ባትሪ ከ33W ሱፐር ቻርጅንግ ሲስተም እንዳለውና በአጭር ጊዜ 100% ባትሪ ቻርጅ ማድረግ አቅም ያለው የስልክ ሞዴል ነው- ብሏል ኩባንያው ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ፡፡

በዚህ በምረቃ ወቅት ንግግር ያደረጉት የቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ ብራንድ ማኔጀር አቶ ኤሊክ ኋንግ፤ ‘’ይህ በላቀ ቴክኖሎጂ በልዩ መልክ የተመረተውን አዲሱ spark 20 pro+ በዚህ አህጉራዊ ውድድር ወቅት በማስተዋወቃችን ኩራት ይሰማናል። በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ እየጨመረ የመጣውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት አለም ከደረሰበት የስማርት ስልክ ቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር፣ የአህጉሪቷን እድገት ለማፋጠን ለሚደረገው ርብርብ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን አንጠራጠርም። ከዚም በተጨማሪ ድርጅታችን ቴክኖ ሞባይል ተወዳጅ የሆነውን አዲሱን ስፓርክ (spark 20 pro+) ስልክ ከማስተዋወቅ ባለፈ የብዙ እግር ኳስ ከዋክብት መፍለቅያ በሆነችው አፍሪካ የ2024ቱን የአፍሪካ የእግር ኳስ ዋንጫ ይፋዊ ስፖንሰር በመሆኑ ደስታችን ላቅ ያለ ነው።’’ ብለዋል።

Read 423 times