Saturday, 10 February 2024 10:05

አርኪ የሪል እስቴት ኤክስፖ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

”ይህን ሳያዩ ቤት እንዳይገዙ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ አርኪ የሪል እስቴት ኤክስፖ፤ ከየካቲት 15- 17 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ  እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ በዚህ ኤክስፖ ላይ ሪል እስቴት

አልሚዎች ቤት በማቅረብ ሲሳተፉ፣ ባንኮች ደግሞ ፋይናንስ በማቅረብ እንደሚሳተፉ አዘጋጆቹ ጠቁመዋል፡፡በኢንቴርየር ዲዛይን (ቤት የማስዋብ አገልግሎት) የተሰማሩ እንዲሁም የእንጨት ሥራ ውጤቶችን የሚያቀርቡ

ፈርኒቸር ቤቶችም በኤክስፖው ላይ እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡ ዘርፉ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝም በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ሌሎች የኤክስፖው ድምቀት ናቸው ተብሏል፡፡ በዚህ ኤክስፖ አቅምን ታሳቢ በማድረግ

ታላቅ ቅናሽ ያደረጉ ሪል እስቴቶችም እንደሚሳተፉ የኤክስፖው አዘጋጆች ጠቁመዋል፡፡ኤክስፖው ይህን ሁሉ በአንድ ቦታ በማካተት የቤት ፈላጊውን ራስ ምታት ያቀላል የሚሉት አዘጋጆቹ፤ ቤት መግዛት የሚፈልግ

ዋጋንና ጥራትን እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን ለማሰባሰብ የሚያባክነውን ጊዜና ጉልበትም ይቆጥባል ባይ ናቸው፡፡  ከ70 በላይ ድርጅቶች የሚሳተፉበትን ይሄን ኤክስፖ እስከ 10ሺ የሚደርሱ ሰዎች እንደሚጎበኙት

ይጠበቃል ብለዋል፤ አዘጋጆቹ አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር፡፡ አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ”አርኪ ሆምስ“ ኤክስፖን ሲያዘጋጁ፣ የዘንድሮው ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል፡

Read 360 times