Saturday, 10 February 2024 10:09

ፐርፐዝ ብላክ 6 የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎችን አስተዋወቀ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በቅርቡ 16 እህት ኩባንያዎችን እንደሚከፍት ተጠቁሟል
* በቀጣዮቹ ወራት 24 የቴክኖሎጂ ፕላትፎርሞችን ተደራሽ ያደርጋል

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ፤ ከገበሬው ቴክኖሎጂ ሶሉሽን የተሰኘ እህት ኩባንያ በመመሥረት ስድስት የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎችን አስተዋወቀ፡፡ TርTዝ ብላክ፤ የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎቹን ያስተዋወቀው ከትላንት በስቲያ ሐሙስ ሰንጋተራ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ውስጥ በተዘጋጀው ከገበሬው ቴክኖሎጂ ሶሉሽን  የምረቃ ሥነስርዓት ላይ ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መሥራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ፣ ኩባንያው ያበለፀጋቸውን ስድስት የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎችን ያስተዋወቁ ሲሆን፤ ፐርፐዝ ብላክ በቀጣይ ወራት 24 የቴክኖሎጂ ፕላትፎርሞችን ተደራሽ እንደሚያደርግም አብስረዋል፡፡
ኩባንያው ትኩረቱን ቴክኖሎጂ ላይ ያደረገበትን ምክንያት ያስረዱት ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ፤ የTርTዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትልቁ ዓላማው፣ የጥቁር ህዝቦች ኢኮኖሚ ልህቀትን መፍጠር በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
“TርTዝ ብላክ ኢትዮጵያ የንግድ አክሲዮን ማህበር፣ በዓለማቀፍ ደረጃ በጥቁር ህዝቦች ላይ ለዘመናት የቀጠለውን አድሎአዊ ሥርዓት በቢዝነስ ሞዴል በሚረጋገጥ የኢኮኖሚ የበላይነት ለማመዛዘን የተቋቋመ ኩባንያ ነው፡፡” ተብሏል፡፡
ባለፈው ሐሙስ በተካሄደው የከገበሬው ቴክኖሎጂ የምረቃ ስነስርዓት ላይ ስድስት የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች የተዋወቁ ሲሆን፤ ኩባንያው ከዚህ ቀደም ኢ-ኮሜርስ ማስተዋወቁ ይታወሳል፡፡በከገበሬው ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አማካኝነት ከተዋወቁት መተግበሪያዎች ውስጥ “የከገበሬው የግብርና ምርቶች አቅርቦት” መተግበሪያ አንዱ ሲሆን፤ ገበሬው ከሸማቹ ጋር የሚገናኝበት መድረክ ነው ተብሏል፡፡“ገበሬዎች ምርታቸውን ከሸማቹ ጋር ማገናኘት አለመቻላቸው ነው ድሃ አድርጎ ያስቀራቸው” ያሉት ዶ/ር ፍስሃ፤ ይሄ የቴክኖሎጂ መተግበሪያ  ገበሬውን ከሸማቹ ጋር ያገናኘዋል ብለዋል፡፡
ሌላኛው መተግበሪያ “የከገበሬው ኮንስዩመር ብድር ማኔጅመንት” በሚል የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህም ሸማቹ የብድር አገልግሎት የሚያገኝበት መድረክ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሦስተኛው የቴክኖሎጂ መተግበሪያ የኢ-ለርኒንግ አስተዳደር ሥርዓት ነው ተብሏል፡፡ ከገበሬው ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ምረቃን አስመልክቶ የተሰራጨው መረጃ እንደሚገልፀው ይህ መተግበሪያ፤ “በተለያዩ የትምህርት መስኮችና ከ77 በላይ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የክህሎት ማበልፀጊያ ሥልጠናዎችን በበይነ መረብ አማካኝነት ባሉበት ሆነው መከታተልና አቅምን ማጎልበት የሚቻልበት ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በተለያየ መስክ እውቀትና ችሎታ ያላቸው ግለሰቦችም ዕውቀታቸውን የሚያጋሩበት ድረ ገፅ ነው፡፡” ከእነዚህ በተጨማሪ “የከገበሬው ቴሌቪዥን መረጃ ማሰራጫ”፣ እንዲሁም “የከገበሬው ኦርደር እና ዴሊቨሪ መቆጣጠሪያ” እና ሌሎች መተግበሪያዎች በምረቃ ሥነስርዓቱ ላይ ተዋውቀዋል፡፡
ኩባንያው በጥቂት ወራት ውስጥ የቴክኖሎጂ ፕላትፎርሞቹን ቁጥር 24 እንደሚያደርስ ያስታውቁት የፐርፐዝ ብላክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ የኛ ዓላማ እነዚህን ፕላትፎርሞች የሁሉም የመገልገያ መድረክ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡
TርTዝ ብላክ ኢትዮጵያ በሁለት ዓመት ውስጥ አድጎና አዋቂ ሆኖ ልጅ ለመውለድ በቅቷል ያሉት ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ፤ በቅርቡም 16 እህት ኩባንያዎችን እንደሚከፍት አስታውቀዋል፡፡
 ራዕዩ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ተቀዳሚ የግብርና ምርት አቅራቢ መሆን እንደሆነ የሚገልፀው TርTዝ ብላክ፤ ተልዕኮው ደግሞ በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነትን ታሪክ ማድረግ እንዲሁም ኢትዮጵያ ለሌሎች የአፍሪካ አገራትና ጥቁር ማህበረሰብ ለሚገኝባቸው አገራት የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የተነሳሽነት ምንጭና አርአያ መሆን ነው ይላል፡፡ 

Read 436 times