Saturday, 10 February 2024 10:11

60ኛው ዓመታዊ የህክምና ጉባኤና ዓለማቀፍ የጤና አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በ4 ዘርፍ ሽልማቶችን ይሰጣል
በጉባኤው ከ100 በላይ ድርጅቶች ይሳተፉበታል ተብሏል



60ኛው ዓመታዊ የህክምና ጉባኤና ዓለማቀፍ የጤና አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በ4 ዘርፍ ሽልማቶችን ይሰጣል
በጉባኤው ከ100 በላይ ድርጅቶች ይሳተፉበታል ተብሏል

ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችል ጤናማና የበለፀገ ማህበረሰብ የማየት ራዕይ ያነገበው የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር፣ ዘንድሮ 60ኛውን ዓመታዊ የህክምና ጉባኤና ዓለማቀፍ አውደ ርዕይ፣ ከየካቲት

29-30 ቀን 2016 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡
ዓመታዊው የህክምና ኮንፈረንስ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩ ዕውቅ የህክምና ባለሙያዎች ያላቸውን ዕውቀት፣ የምርምር ግኝቶችንና የህክምና ልምዶችን ለመለዋወጥ የሚረዳ መድረክ መሆኑን የገለፀው

ማህበሩ፤ የፓናል ውይይቶችም እንደሚካሄድበት ጠቁሟል፡፡
በህክምና ጉባኤው የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናዎች እንደሚሰጡና የሳይንሳዊ ግኝቶች የሚቀርቡበት ክፍለ ጊዜም መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር 60ኛው ዓመታዊ የህክምና ጉባኤና ዓለማቀፍ የጤና አውደ ርዕይ ላይ ከ600 በላይ የተከበሩ የህክምና ባለሙያዎች፣ ከተለያዩ ክልሎች የሚመጡ የማህበሩ አባላት ተወካዮች፣ የተለያዩ

የጤና ባለሙያዎች ማህበራትና ስፔሻሊስቶች ማህበራት የተውጣጡ ተወካዮች እንዲሁም የህክምና ኮሌጅ ሃላፊዎች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡
በአውደርዕዩ ከ100 በላይ ድርጅቶች እንደሚሳተፉበትና ከ2ሺ በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ማህበሩ ጠቁሟል፡፡ በየዓመቱ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር የሽልማት መርሃ ግብርም በአራት

ዘርፎች እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ ሽልማቶቹም፤ “የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የዓመቱ ምርጥ የህክምና ተማሪዎች ሽልማት 2016”፣ “የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የህይወት ዘመን ሽልማት 2016”፣”የኢትዮጵያ

ሕክምና ማህበር ተፅዕኖ ፈጣሪና ምርጥ ወጣት ሃኪም ሽልማት 2016” እና “የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የ2016 የዓመቱ ምርጥ ተቋም” ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የሕክምና ማህበር የተመሰረተው በ1954 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡

Read 439 times