Tuesday, 05 March 2024 00:00

የመጽሐፍ ቅዱስ ሳምንት" ለአምስት ቀናት ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(0 votes)
• ቅዱሳት መጻሕፍት በቅናሽ ዋጋ ለምእመናን ይቀርባሉ ተብሏል
“መጽሐፍ ቅዱሳዊ እሴቶችን በሕዝባችን ሕይወት እናሥርጽ!” በሚል መሪ ቃል፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ሳምንትና የቅዱሳት መጻሕፍት ዐውደ ርዕይ ከመጋቢት 16 እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር በዛሬው ዕለት ጠዋት በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ሳምንት ለአምስት ቀናት እንደሚካሄድ አስታውቋል።
በዚህ መርሐ ግብር ላይ የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፣ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ፣ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ተቋማትና በርካታ ቁጥር ያላቸው ምእመናን በስፋት እንደሚሳተፉበት ተነግሯል፡፡
98 ዓመት እድሜ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ሰብሳቢ ዶ/ር ተስፋጽዮን ደለለው እንደገለጹት፤ ማኀበሩ 22 በሚደርሱ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መጽሐፍ ቅዱስ በማስተርጎም ላይ ሲሆን በቀጣይ ከ20 በላይ በሚደርሱ ተጨማሪ ቋንቋዎች አስተርጉሞ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በአውደ ርዕዩ ላይ ቅዱሳት መጻሕፍት በቅናሽ ዋጋ ለምእመናን እንደሚቀርቡ የተገለጸ ሲሆን፤ ምዕመናን በተጠቀሱት ቀናት ያለምንም ክፍያ ወደ ስካይ ላይት ሆቴል በመምጣት በስጋም በነፍስም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማህበሩ ጥሪ አቅርቧል።
በመርሐ ግብሩ ማጠናቀቂያ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የመጽሐፍ ቅዱስ ቀን በሚል የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

   የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
Read 459 times