Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 29 September 2012 10:02

ለ64ኛው ኤሚ አዋርድ ትልልቅ ተዋናዮች ተሸለሙ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ64ኛው የኤሚ አዋርድ ትልልቅ ተዋናዮች ለሽልማት መብቃታቸውን ሮይተርስ ገለፀ፡፡ በኤቢሲ ቻናል የተላለፈውን የሽልማት ስነስርዓት 21.9 ሚሊዮን አሜሪካዊያን ተከታትለውታል፡፡ ለኤሚ ሽልማት ከበቁ ታዋቂ ተዋናዮች መካከል ኬቨን ኮስትነር፣ ኦስተን ኩቸር እና ጁሊያኔ ይገኙበታል፡፡ የኤሚ አዋርድ ለቴሌቭዥን መዝናኛ ኢንዱስትሪው የላቀ ብቃት ለሰጡ ባለሙያዎችና ስራዎቻቸው የሚሰጥ ልዩ ሽልማት ነው፡፡ በ64ኛው የኤሚ አዋርድ በኤቢሲ ጣቢያ የሚታዩት ሁለት ተከታታይ ፊልሞች “ሞደርን ፋሚሊ” እና “ሆም ላንድ” ከፍተኛ ተሸላሚ ለመሆን ሲበቁ በ17 የሽልማት ዘርፎች ታጭቶ አንድም ጊዜ መሸለም ያልቻለው “ሜድ ሜን” የተባለው ፊልም አሁንም ሳይቀናው ቀርቷል፡፡

“ሆም ላንድ” የተባለውና በኤቢሲ በተከታታይ የሚቀርበው ድራማዊ ፊልም ለኤሚ አዋርድ ለሁለቱም ፆታዎች ምርጥ የድራማ ተዋናዮችን፣ በምርጥ የድራማ ጽሑፍ ተሸላሚ ሲሆን “ሞደርን ፋሚሊ” የዓመቱ ምርጥ ኮሜዲ ፊልም እና ሌሎች ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡

“ሃትፊልድና ማኮዲስ” በተባለ ታሪካዊ ፊልም የተወነው ኬቪን ኮስትነር የዓመቱ ምርጥ የቲቪ ፊልም ተዋናይ ተብሎ ሲሸለም በሴቶች ዘርፍ ተመሳሳይ ሽልማት ያሸነፈችው “ጌም ቼንጅ” በተባለ ፊልም ላይ የተወነችው ጁሊያና ሙር ናት፡፡ በ64ኛው የኤሚ አዋርድ ላይ የዓመቱ ምርጥ የሪያሊቲ ፕሮግራም ተብሎ የተሸለመው በሲቢኤስ ቻናል የሚተላለፈው “ዘ አሜዚንግ ሬስ” ሲሆን የዳንሲንግ ዊዝ ዘስታርስ አቅራቢ ቶም ቤርጌውን የዓመቱ ምርጥ የሪያሊቲ ሾው አቅራቢ ሆኖ አሸንፏል፡፡

 

 

Read 2672 times Last modified on Saturday, 29 September 2012 10:03