የቻይና ባህል ሚኒስትር በህገወጥነት የፈረጃቸው ከ100 በላይ ሙዚቃዎች በቻይና እንዳይሰራጩ የሰጠው ቀነ ገደብ አንድ ሳምንት የቀረው ሲሆን የአርቲስቶቹ ዌብሳይቶች እንዲዘጉም ተወስኗል፡፡ በቻይና ሙዚቃ ኢንዱስትሪ በየዓመቱ ከ100 በላይ አልበሞች እንደሚሰራጩ ሲታወቅ ገበያው እስከ 179 ሚሊዮን ዶላር ይንቀሳቀስበታል፡፡
የቻይና የባህል ሚኒስትር የባህል ደህንነትን አደጋ ላይ ይጥላሉ ያላቸውን ከ100 በላይ ዘፈኖች በአገሪቱ እንዳይሰራጩ እገዳ መጣሉን ሲኤንኤን ዘገበ፡፡
የቻይና መንግስት በሳንሱር ያልታዩና በይፋ ምዝገባ ያልተደረገላቸው ዘፈኖች በቀጥታ ከኢንተርኔት የሚገበዩበትን ሁኔታ በመቃወም እገዳውን የጣለ ሲሆን ማዕቀቡ ዘፈኖቹ ከያዙት ጭብጥ ጋር የተገናኘ አለመሆኑን ገልጿል፡፡ በቻይና የባህል ሚኒስትር ከታገዱ 100 ዘፈኖች መካከል ታይዋን፣ ሆንግ ኮንግና ጃፓን የተለቀቁት አብዛኛውን ድርሻ ቢወስዱም የቢዮንሴ፣ የካናዬ ዌስት፣ የሌዲ ጋጋ እና የኬቲ ፔሪ የሙዚቃ ሥራዎች በዝርዝሩ መካተታቸውን የሲኤንኤን ዘገባ አመልክቷል፡፡