የግጥም ጥግ
“አገር ውዝግብ ውስጥ ስትወድቅ የማይናድ የሚመስለው ይናዳል። ከድጡ ወደ ማጡ ይሄዳል። “ወጣ ወጣና እንደ ሸንበቆ፣ ተንከባለለ እንደ ሙቀጫ” ያሰኛል። ህዝብ መሪዎች ላይ እምነት ያጣል። ሰላም ሰላም-የሚለው ሁሉ ትርምስና ሁከት ይሰማዋል።“
Read 830 times
Published in
የግጥም ጥግ
(በድሉ ዋቅጅራ) (በድሉ ዋቅጅራ)ወንድምን ከወንድሙ ቢለዩት፣ አልቦ ስጋ - ደም፣ ነፍስም አልቦ፤ጮጮ ላይሞላ፣ ታልቦ ታልቦ፤ልምሻ ሊጥለው፣ አቅም ሰልቦ፡፡ወልነት ያጣው፣ የኛም ቃል፤ሲዘረጋ ይጠቀለላል፤ሲያወፍሩት፣ ደርዙ ይሰላል፡፡የሰው ልጅ ንፉግ ህይወቱን፣ ለነገ ቸርነት ሲያጨው፤ያልተጨበጠ ድንግዝ ምኞቱን፣ በዛሬ ብርሀን እያየው፤ተስፋ አለና ሰየመው፡፡ችግሩ ከተስፋችን ስር፣ ያቆጠቆጠው…
Read 933 times
Published in
የግጥም ጥግ
ተኖረና – ተሞተ“ሳለ – ለሌለ”እየታለ . . . እየተሌለበመሸ – ነጋ – መሸእንደነበረ . . . እንዳለእንዳደረ . . . እንደ – ዋለእንዲሁ . . . እንደ – ዋተተ“መኖር”ን እንደ – ሞገተ“ኗሪ” ሳይኖር . . .ኖረ . . . ኖረና…
Read 833 times
Published in
የግጥም ጥግ
በየጧት ይመጣልማለዳ ይመጣልአዳዲስ እንግዳ!ለሰው ፀጉረ-ልውጥ ለሀገሩ ባዳ።እንደ ለሰው-ማሰብ ያለ አዲስ እንግዳእንደ ጭንቀት ያለ አዳዲስ እንግዳእንደ ሀሴት ያለ አዳዲስ እንግዳእንደ ሀዘን ያለ ቅስም እንደመስበርወይ እንደብልግናወይ እንደማቀርቀርድንገት ሳይጠበቅ ከተፍ የሚል ሀሳብአዳዲስ እንግዳ፣ ለቀልብ የማይቀርብቀን በቀን ማለዳሁሉም ይመጣሉ!በል ተቀበላቸው!ያዘን ማ´ት ቢሆኑም፤ ቤትን የሚያፈርሱንብረት…
Read 734 times
Published in
የግጥም ጥግ
እንደ ሐገር ባህል ልብስ~አምሮ እንደ ተሠፋያኖረን አስውቦ~ህብረ ቀለም ሰጥቶ~ፍቅር እምነት ተስፋእንደ ጉም ብን ብሎ~ሳናውቀው ከጠፋበየእምነት በዐሉ~አንድ ማዕድ ተቋድሰንበልተን ካደግንበት~ ፍቅር ተጎራርሰንነገር ሳይሆን እሳት~ ተጫጭረን ፍሙንየጉርብትናን ልክ~ የጎረቤት ጥቅሙንካጣጣምነበት ደጅ~ የአብሮ መኖር ጣዕሙንበሰልፍ የመረጥነው~ የጣልንበት ተስፋቤት መስጊድን ማፍረስ~እስኪደርስ ከከፋዝናብ ፀሀይ ንቀን~በሠልፍ…
Read 934 times
Published in
የግጥም ጥግ
ፍቅር ለቆሸሸውተስፋ ለሟሸሸውቀን በእድል ደመናሳይነጋ ለመሸውየሳቅን ውብ ኪነትሀዘን ላበላሸው...እንባ ወዴት ወዴትወዴት ነው ‘ሚሸሸው?ልብ ለጠበበው ልብ ለጨነቀውሳግ ለተጋለበው፣ እልህ ለታመቀውሕይወት ለመረረ፣ ቅስም ለደቀቀውከዐይኖች የሚፈልቀውፈልቆ የሚርቀው?እንባ አያሌው ሞኙን፣ ማነው ያታለለው?ልብህን ሽሽና፣ ነፃ ላውጣህ ያለውካይን አርያም ቁልቁል፣ ወዳፈር የጣለውበመራቅ መፍትሄ... በመራቅ ስርየት፥ ያለ…
Read 1503 times
Published in
የግጥም ጥግ